Capture

የፀደቀው ስልታዊ ዕቅድ እና ተቋማዊ ተሀድሶ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የቦርድ አመራር በተዘጋጀው የኮሚሽኑን የ10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ላይ በጥልቀት በመወያየት በሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 9 እና 10 በነበረው የኮሚሽኑ ቦርድ ስብሳባ ላይ ስልታዊ ዕቅዱን አጽድቀዋል፡፡

ይህ ይፋ የተደረገው ስልታዊ ዕቅድ የልማቱን እና የቤተ ክርስቲኒቱን የመንፈሳዊ እና ሰብዓዊ አገልግሎት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጋር በማጣጣም ማህበረሰብ ላይ ተፅእኖ የሚፈጥር መሆኑን  የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ም/ክ ፕሬዝዳንትና የኮሚሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ እንዲሁም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ ሚያዝያ 9 እና 10 /2018 ዓ.ም. በጉዲና ቱምሳ ማሰልጠኛ ማዕከል በተደረገው ጠቅላላ የቦርድ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል ፡፡

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ አቶ ታምሩ ባሀጋ “ዘመን ተሻጋሪ አገልግሎት ማለት የእግዚአብሔርን ሐሳብ ማገልገል ነው” በማለት የእግዚአብሔርን ቃል መልዕክት አካፍለዋል።

በመቀጠልም ለቦርዱ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ቦርድ ሰብሳብ እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ ይህኛው የቦርድ ስብሳባ በጣም ታሪካዊ እና የተለየ የሚያደረገዉ  የኮሚሽኑ 10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ተወያይተን የምናጽድቅበት እና የቤተክርስቲያኒቱን የ100 ዓመት ክብር በዓል ለማክበር ዋዜማ ላይ መሆኑ ነዉ፡፡ በዚህ ሁኔታ አዲሱን ምዕተ ዓመት በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀውን ይህን የኮሚሽኑን ስልታዊ ዕቅድ ማጹደቅ ታሪካዊ ያደረገዋል ብለዋል፡፡

አክለውም የቤተ ክርስቲያኑ የልማት ስራ የወንጌል አገልግሎት መሆኑን በማንሳት እንዲሁም ዕቅዱ የቤተ ክርስቲኒቱን የመንፈሳዊ አገልግሎት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጋር በማቀናጀት ማህበረሰብ ላይ ተፅእኖ የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ስልታዊ ዕቅድም ተቋማዊ ተሀድሶ/ሪፎርም እነዲያመጣ ተስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀደም ሲል በተለያዩ ሁለንተናዊ አገልግሎቶች በሀገር ደረጃ  ሲታገለገል መቆየቷን ገልጸው በልማት ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች እንደ ሀገር የሚታሰቡ መሆናቸውን  አስረድተዋል ። ይህንን ስራ በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል የቦርድ ስብሰባ አስፈላጊነቱን ጠቅሰዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ በበኩላቸው ዕቅዱን ለቦርዱ አባላት በዝርዝር አቅርበው፣ የሚተገበረው ስትራቴጂ “ሁለንተናዊ ለውጥ ያገኙ የማይበገሩ ማህበረሰቦች” የሚል ራዕይ መሠረት እንዳለው አስታውቀዋል። ዕቅዱ ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ልማትን በአንድ አቅጣጫ ላይ ለማስቀመጥ የተነደፈ መሆኑ ተገልጿል።

አክለዉም በዕቅዱ መሠረት እ.ኤ.አ ለ2026–2035 ዓ.ም. ብቻ ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን አስታውቀው ይህም በተቋሙ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ አብራርተዋል ዕቅዱ በተቋማዊ ብቃት፣ በማህበረሰብ ልማት፣ በሰብአዊ እርዳታ እና በፕሮግራም ጥራት ላይ የሚያተኩር ነው ብለዋል ፡፡

ከታቀዱ ዋና ዋና ግቦች መካከል፦

•  ቤተሰቦችን የምግብ ዋስትና ማስገኘት

•  ወጣቶችን በክህሎት ማብቃት

• የሴቶች የአመራር ተሳትፎን ወደ 30% ማሳደግ

• ዲጂታል አሰራር ማስፈን

እንዲሁም ኮሚሽኑ የሀብት ማሰባሰብ ንቅናቄ በማድረግ 25% ገቢ ከአገር ውስጥ ምንጮች ለማግኘት እንደሚሰራ አስታውቋል ይህም ከለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ በተጨማሪ የኮሚሽኑ አቅም እንደሚያጠነክርና አለአስፈላጊ ጫና እንደሚቀንስ ተጠቁመዋል ።

አጠቃላይ የቦርድ ስብሳበው የኮሚሽኑን የ1ዐ ዓመት ስልታዊ ዕቅድና በጀት  እንዲሁም እ.ኤ.አ የኮሚሽኑ ጽ/ቤት 2ዐ25 የስራ እድገት ሪፖርት ቦርድ እንድሰሙ የተደረገ ሲሆን ተሻሽሎ በቀረበው በኮምፓሽን በሚረዱ ልጆችና ወጣቶች ፕሮጀኽቶች ማኑዋል መርምረዉ አጽድቀዋል፡፡ በተጨማሪ  የተጠፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ስጋት መቀነስና ዝግጁነት፣ ልማትና የቤተክርስቲያን ቅንጅታዊ አሰራር፣   ሀብት ማሰባሰብና ሎካላይዜሽን ሰፍ ውይይት በማድርግ የወደፊት አቅጣጫ ለማሰቀመጥ ዕቅድ ተይዟል፡፡

ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ወይታ ወዛ በበኩላቸው ʺ የወንጌል በር የሚሆኑ ስራዎችንʺ በመስራት ምስክሮች መሆን አለብን በማልት አሳስበዋል፡፡

እንዲሁም በኮሚሽኑ ቦርድ አባል በመሆን ቀደም ባሉ ጊዜያት ያገለገሉና የአገልግሎት ዘመናቸውን ለጨረሱ መጋቢ አለሙ ኤርጋጎ የጸሎትና የምስጋና የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *