photo_9_2025-05-02_12-13-03

የኮሚሽኑ የአዳማ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረት አድሱን የስራ ቢሮ መረቆ ከፈተ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የአዳማ ከተማ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረት አድሱን የስራ ቢሮ መረቀ፡፡ ይህም ጥምረቱም በትናንትናው ዕለት በአዳማ ከተማ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሁለ-ገብ ማዕከል በተዘጋጀው የምስጋና ሁነት ላይ ነው የተከናወነው፡፡

የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረት በ8 ሚሊዮን በሚገመት  ብር ለብሮ አገልግሎት የገዙትን ብሮ በትናንትናው ዕለት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ተሎሬ እና በሸርትረስት የአፍሪካ ፕሮግራሞች መሪ አሪኖላህ ኤልዛቤት – በጋራ በመሆን የተገዘውን ብሮ ሪቫን በመቁረጥ መሪቀው ከፍተዋል፡፡

በምስጋና እና ምረቀውም ፕሮግራም ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ የሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ከቲርፈንድ ጋር በመሆን የራስ አገዝ ቡድን ልማት አሰራር – ተሞክሮን ከህንድ አገር በማምጣት በ1994 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ አምስት የራስ አገዝ ቡድኖችን በማደራጀት ስራ ማስጀመራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉትን የሕብረተሰብ – ክፍሎች ከድህነት ለማላቀቅ በራስ አገዝ ቡድን በማደራጀት፤ በማስፋፋትና በማጠናከር በአዳማ እና በአካባቢዋ በረካታ ስራወዎችን ሲሰራ ቆይቷል:

የቡድኖችም እንቅስቃሴ ብዙ ፈተናዎችን በማለፍ አሁን ላይ ብዙዎችን ከድህነት ከማውጣት ባሻገር ተቋም መመስረት እንዲችሉም  አቅም መፈጠር የቻለ የልማት ፅንሰ ሀሳብ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ገልጸው አሁንም ብሆን የደረስንበት አድስ ስራ የሚንጀምርበት እንጂ ስራ የጨረስንበት አይደለም ስሉ በምስጋና ለተገኙ ለጥምረቱ አባላት እና በለድርሻ አካላት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በራስ አገዝ ቡድን ስራ የተቀዳጀነው ስኬት ትልቅ ነው ነገር ግን የአድስ ጅማሮ አድስ ምዕራፍ ነው፡፡

በሸርትረስት የአፍሪካ ፕሮግራሞች መሪ አሪኖላህ ኤልዛቤት በበኩሏ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረት ለማህበረሰብ መረ ልማት ብቁ ምስክር ናቸው፡፡ ይህ እውን እንዲሆን እያደረጉ ያሉ አጋር አካላት ማለትም፡ የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ የሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን፣ ቲሪፈንድ፣ ሸረትርስት፣ ዋራንዴ አድቫይዜሪ ማዕከል እና የተለያዮ መንግስት በለድረሻ አካለት ሚና ከፍ ያለ ነው፡፡ አሁንም ማህበረሰብን ወረደን የሚናግዝበት ግዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን መሰል ስራ ለመስራት በብዙ ፍለጋ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖችን መግኘት ቻልን ያሉ ሲሆን ልማት የሚቆም ነገር አይደለም በተላይ ማህበረሰብ መረ ልማት ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኮሚሽኑ የማህበርሰብ ኑሮ ማሻሻያ እና ማቋቋሚያ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በውስጡ በረካታ የልማት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን የያዘ ሲሆን ለአብነትም የአስቸኮይ ጊዜ እርዳታ እና መልሶ ማቋቋም፣ የግብርና፣ የራስ አገዝ ቡድን ልማት፣ሰላም ግንባታ  ፕሮጀክቶች የስራ አፈጻጽምም በስብሳበው እንደሚቀረብ ይጠበቃል፡፡

ለራስ አገዝ ቡድን ማደግ እና መጠንከር ለበረከቱት ለተለያዮ አካለት/ ተቋማት እና አመራር/ግለሰቦች የምስጋና እና የእውቅና  ሰርቲፍኬት ተበረክቶላቸዋል፡፡

አቶ ድንቁ ሹሚ በኮሚሽኑ የማህበርብ ኑሮ ማሻሻያ እና ማቋቋሚያ ፕሮግራም ዳይሬክተር በበኩላቸውም ይህ የራስ አገዝ ቡድን ልማት እንቅስቃሴ መህበረሰብ መር ልማት በመረጋገጥ ረገድ የጎላ አስተዋጾ እያደረገ ነው፡፡ ልማት ኮሚሽን እና ቲረፈንድ የቡድኖችን እንቅስቃሴ ከመመስረት እስከ መደገፍ ድርስ ለለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን አሁን ላይም የአዳማ ከተማ የራሰ አገዝ ቡድኖች ከ ShareTrust, Warande Advisory Centre (WAC) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በኮሚሽኑ ጥላ ስር ሆነው ለሶስት ዓመት የሚቆይ   በ1.5 ሚሊዮን ዶላር በረካታ  የልማት ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

የአዳማ ከተማ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረትም እራሱን የቻለ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ቦጎ አድራጎት ድርጂት ሆኖ በአዋጂ ቁጥር 1113/2011 አንቀ57(1) አገር በቀል ድርጂት ሆኖ በሰርቲፍኬት ቁጥር 7580 ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስቪል ማህበረሰብ ድርጂቶች በለስልጣን ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት ተሰጥቶታል፡፡

አሁን ላይ የራስ አገዝ ቡድኖች ብዛት 273፣ የማህበራት ብዛት ዳግሞ 27 እና  3 ጥምረቶች ያሉት ሲሆን  ጠቅላላ የራሰ አገዝ የአበላት ብዛት ደግሞ 10800 ነው፡፡ የራስ አገዝ ቡድኖች ጠቅላላ ቁጠባ ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ስሆን አጠቃላይ ከፕታላቸው ደግሞ 83.5 ሚሊዮን  ብር ነው፡፡

የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረት በጎ አድራጎት ድርጅት ድርጅታዊ አቅሙን ከመገንባት ባሻገር ለአባላቱ የብድር እና የሙያ ት/ት በማመቻቸት የአበላቱን እኮኖሚ እያሳደገ ነው፡፡ ማህበረሰብ መረ ልማት እና እድገትን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ በከብት እና ዶሮ እርባታ፣ በፀጉር ሙያ፣ ድኮር እና ምግብ አዘገጃጀት፣በእንጨት እና በጋርመንት ሙያ በእያንዳንዱ ዘረፍ 22 ተማሪዎችን እየስተማሩ ሲሆን፣የእህል መጋዝን በመክፈት፣ በአማረኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የመሰረተ ትምህርት በመስጠት፣ ልጆችን የጤና፣ንጽህና አጠባበቅን መስተማረ እና የንጽህና መጠበቅያ ግብዓቶችን በመደገፍ በርካታ የአቅም ግንባታ እና የማህበረሰብ ልማት ስራዎችን ጥምረቱ እየከወነ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለትም ከሚመለከታቸው የፌድራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት በለድርሻ አካላት ጋር በፕሮጀክቶች ዙረያ የውይይት እና የምክክር ግዜ እየተደረገ ሲሆን በነገውም ዕለት የፕሮግራሙን ዓመታዊ የስራ አፈጻጽም ርፖርት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

Facebook: https://www.facebook.com/The-Ethiopian-Kale-Heywet-Church-Development-Commission-106866628784650

Youtube : https://www.youtube.com/@ekhcdc8366

Telegram : http://t.me/EKHCDCofficial

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *