photo_2025-02-27_15-04-06

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን በወቅታዊው የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ውይይት አካሄዱ   

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ም/ፕሬዝደንትና የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ ፤ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ እና  የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን  የሰባዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን  ም/ክ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ኢንጅነር ንጋቱ ጫፎ   የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን እና ልማት  የማይነጣጠሉ  መሆናቸውን  በተለይም ከሕይወት ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጽዋል፡፡ 

 የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን እና ልማት  የማይነጣጠሉ  መሆናቸውን እንዲሁም ልማቱ  ከቤ/ክንቱ ምስረታ ጋር እንደተጀመረ  አላማውም  ፍቅር እና ፍጥረትን ሁሉ በክርስቶስ ልብ ማገልገል እንደሆነ  የወቅቱን አጠቃላይ  የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን አጠቃላይ እንቀስቃሴ  በውይይታቸው ወቅት የቤተክርሲቲያንቱ ም/ፕረዝዳንት እና ኮሚሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ አብራርተዋል ።

እንዲሁም ከጥር 25-27/2017 ዓ.ም ጀምሮ የኮሚሽኑ ማኔጅመንት፣ የ ቦርድ አመራሮች በድሬዳዋ እና ሀረር ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን  ጋር የነበራቸው ቆይታ እና በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ  ሚደጋቶላ ወረዳ የሚሰራውን  የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት  ስራዎችን ጉብኝት ማድረጋቸው ውጤታማ  መሆኑን  የኮሚሽኑ ም/ክ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ኢንጅነር ንጋቱ  ጫፎ    አብራረተዋል ። የልማት  አገልግሎቱን  ሀገር በቀል ለማድረግ  ከፍተኛ ጥረት የተደረገ መሆኑን በረጂ ድርጅቶች  ላይ ብቻ መደገፍ እንዲቀር እየተሰራ  መሆኑን  አክለዋል፡፡

እንዲሁም ቀድሞ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን  ልማት ኮሚሽን  ይባል የነበረው መጠሪያ  አሁን ላይ  የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ተብሎ እንዲጠራ አዲስ ስያሜ መሰጠቱ  የገለጹ ሲሆን  ምክንያቱ  ደግሞ  የልማት ኮሚሽኑ አገልግሎት  በቀጥታ ከሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ጋር  የተያያዘ  በመሆኑ ነው ሲሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ ገልጽዋል፡፡ የማህበረሰቡ  የልማት ተደራሽነት  ለማስፋት  ከፍተኛ ስራ እየተከናወነ  መሆኑን፤  የልማት ስራው  ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ  ጋር  ለማቀናጀት  መጠነሰፊ  ስራ  እየተሰራ  መሆኑን  ጠቁመው በመጨረሻም    የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን   አጋር ድርጅቶች እና የተለያዩ አካላት ስለበጎ አድራጎታቸው እና እያደረጉ ስላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *