በኮሚሽኑ የ10 ዓመት ስልታዊ አቅጣጫ እና በ5 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ፣በቅንጅታዊ አሰራር ማዕቀፍ፣የአደጋ ሥጋት ቅደመ-ዝግጅት፣መንፈሳዊና ሰብዓዊ/ልማትን ለመቀናጀት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠርቶች እና የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ተሞክሮን በተመለከተ ከአጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን፣ከቀጣናዎች እና ሕብረት ለመጡ የየዘርፉ መሪዎች በጅማ ምዕራብ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ማዕከል የምክክርና አወደ-ጥናት ከሐምሌ 24-25/2018 ዓ.ም ተደርጓል፡፡
በአውደ-ጥናቱ የኮሚሽኑ ቦርድ ሳብሳቢና የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ ፣ ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ወይታ ወዛ ፣ ዶ/ር ኢንጂነር ንጋቱ ጫፎ፣ አቶ አብርሃም አላምቦ፣የቦርድ አባላት፣ የሴቶች፣ የወጣቶችና መሪዎችና የልማት አስተባባሪዎች ከምዕራብ ቀጠና፣ኦሞ-ጎጀብ፣ ምዕራብ ደቡብ ቀጠና እና የኮንታ ልዮ ሕብረት መሪዎች ተሳታፈዋል።


የኮሚሽኑ ቦርድ ሳብሳቢና የቤተክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ እንደገለጹት፤ይህ ስልጠና ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትን በተቀናጀ መልኩ እንድታከናውን የሚያስችልና ቤተክርስቲያን ያላትን ሀብት በማውቅ፣በመለየት፣በማደራጀት እና በማልማት ለሰው ልጅ ጥቅምና የእግዚአብሔር መንግስት እንዲሰፋ መስራት ላይ ያለመ አውደ ጥናት መሆኑን ገልጸዋል፡፡


የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ ኮሚሽኑ የ10 ዓመት ስልታዊ አቅጣጫ እና የ5 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባቱ ገልጽው በአውደ ጥናቱ ለተገኙት የተለያዮ ቀጠና ሕብረት መሪዎች የኮሚሽኑን የ10 ዓመት ስልታዊ አቅጣጫ እና የ5 ዓመቱን ዕቅድ በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አደርገዋል፡፡


የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ወይታ ወዛ በበኩላቸውም ስለ ቅንጅታዊ አሰራር ማንዋል ለአወደ-ጥናት ተሳታፊዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ቃለ-ሕይወት ቤተክርስቲያን አሁን በዚህን ጊዜ ነቅታ ወደ ቅንጅታዊ አሰራር መምጣት ለቤተክርሲቲያኒቱ ሁለንተናዊ አገልግሎት አስፈላጊ ሲሆን ከሁሉም በላይ ደግሞ ቅንጅታዊ አሰራርን የእግዚአብሔር ቃል መመሪያ ይሰጣል፡፡ ለዚህ ደግሞ መታዘዝ አለብን የሚል አቋም መያዙን ገልጸዋል።



የኮሚሽኑ የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ደስታ ላምቤቦ በበኩላቸው ይህ አወደ-ጥናት ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ለሁለንተናዊ አገልግሎት መረጋገጥ የውስጥ ሀብትን በተቀናጀ መልኩ ለማሰበሰብ፣ ለማልማት እና ለማስተዳደር የሚታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው ይህ ጥሪ የሁሉም ምዕመናን እና የመሪዎች መሆኑን በመጠቆም፤ እያንዳንዱ አባል ለዚህ ዕቅድ መሳካት እንድጸልይና እንድሰራ ጥሪ አቅርበዋል።





ይህ ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት የኮሚሽኑ ቦርድ አባል አቶ አብረሃም ገሰሰ ይህ ስልታዊ የሀብት አሰበሰብና የማቀናጀት ሥልጠና በትክክለኛ ጊዜ የተሰጠ እና ወደ ተግባር ለመግባት የሚያነሳሳ መሆኑ ተከትሎ የተለያዮ ሕብረቶች እና ቀጠናዎችም ዕቅዱን ለመተግበር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ገልጸዋል፡፡

በኮሚሽኑ የአስቾኳይ ጊዜ እርዳታ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ፕሮግራም ማናጀር አቶ አብርሃም አለምቦ በበኩላችው ቤተክርስቲያን የአስተሳሰብ ለውጥ መድረግ አለባት ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ ሀብት እጥረት የለም የአስተሳሰብ ክፈተት እንጅ ያሉ ሲሆን አክለዉም በለው ነገር በቅንጅት፣በዕወቀት እና በዕቀድ የውስጥ ሀብት መለየት፣ማደራጀት፣ማልማት ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡



በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ምዕራብ ቀጠና ሰብሳቢ ማርቆስ ዱጉማ ልማት እና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለማቀናጀት የተጀመረው ጉዞ መልካም እንደሆነ በመግለጽ እንደ ምዕራብ ቀጠና በዚህ ረገድ በቅንጅት ለመስራት እና ሥራ በህላችንን ለማደበር እና ያለንን ሀብት እንዴት ማልማት እንደምንችል ግንዛቤ ያገኘንበት ስልጠና ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡


መጋቢ ገዛኸኝ ጋሻራ የኦሞ ጎጀብ ቀጠና መሪ በስልጠናው ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት እና ልማትን ለመስራት በሚያስችል የቅንጅት እና የአሰራር ማዕቀፎች ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኙ ተናግረው አወደ-ጥናቱ ቤተክርስቲያን ያላትን ሀብት እንዲታውቅና እንዲትጠቀም ለማድረግ አይን ገላጭ ስልጠና መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


በመጨረሻም ይህ ቅንጅታዊ አሠራር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን በቀጠና፣ በኅብረት እና በአጥቢያ ደረጃ ያሉ መዋቅሮች ተቀናጅተው እንዲሠሩ፣ የአጥቢያዎችን አቅም በመገንባት፣ አሠራሮችን በመዘርጋት እና በማደራጀት የልማት ሥራዎችን የበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የተብራራ ሲሆን በተደረጉ የአወደ-ጥናት መድረኮች ከተሳተፉ የቤተክሪስቲያን መሪዎች የተገኘው ግብረ-መልስ፤ በአካባቢያቸው ያለውን የሀብት አቅም በማየት ሀብት ለማሰባሰብ እና የቅንጅታዊ አሠራርን ተግባራዊ ለማድረግ መንገድ የከፈተ መሆኑን ተጠቅሷል።











Add a Comment