ሃዋሳ፡- ከሰኔ 5-6/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን በመመሪያዎች፣ ስልታዊ ዕቅዶች እና የውስጥ አሰራር ደንቦች በኮሚሽኑ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎች በበላይነት ለመምራትና ለመቆጣጠር የተነደፉ ንድፎች ዙርያ ከቀጣና በተወጣጡ የየዘርፉ መሪዎች በመሀል ደቡብ ቀጣና ሀዋሳ ከተማ በታቦር አጥቢያ ምክክር አካሂዷል።







በምክክሩ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎረ ፣ ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ወይታ ወዛ ፣ ዶር ኢንጂነር ንጋቱ ጫፎ ፣ አቶ አብርሃም አላምቦ ፣ አቶ መሳሪያ ወታንጎ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ሥራ አስፈጻሚ አባል እና በክላስተር ቀጣናዎች የቦርድ አባላት የሴቶች የወጣቶች እና የየቀጣና የልማት አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል።
የኮሚሽኑ ቦርድ ሰፊ ስራ እየሰራ ሲሆን፥ ቤተ ክርስቲያኒቱ መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ ችግሩን በሚፈታ መልኩ፣ ከቃለ ሕይወት አልፎ እንደ አገር ትልቅ ለውጥ በሚያመጣ አቋም ላይ ከፍተኛና ሰፊ ዕቅድ አውጥታ እየሰራች መሆኑን የልማት ኮሚሽኑ ቦርድ አባልና የመሃል ደቡብ ቀጠና ሳብሳቢ አቶ መስሪያ ወታንጎ ተናግረዋል።




አክለውም እግዚአብሔር በእያንዳንዱ አጥቢያ፣ ህብረትና ቀጠናዎች ውስጥ ትልቅ ጸጋ የሰጠ በመሆኑ፥ ከውጪ የሚመጣውን እርዳታ ከመጠበቅ ይልቅ በአካባቢያችን ያለውን ሀብት በጥራት ጥቅም ላይ ማዋልና ክፍተቶችን መልሶ ማየት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶር ተፈራ ተሎሬ ኮሚሽኑ የ10 ዓመት ስልታዊ አቅጣጫ እና የ5 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ በማዘጋጀት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር እና ሀብት መሰባሰቢያ ማኖል በማዘጋጀት እና ማጽደቅ ኮሚሸኑ ወደ ስራ መግባቱ ገልጽው በአውደ ጥናቱ ለተገኙት የተለያዮ ቀጠና መሪዎችም የኮሚሽኑን የ10 ዓመት ስልታዊ አቅጣጫ እና የ5 ዓመቱን ዕቅድ በተመለከተ ሰፍ ያለ ማብራሪያ አደርገዋል፡፡







የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ወይታ ወዛ በበኩላቸውም ቃለ-ሕይወት ቤተክርስቲያን አሁን በዚህን ጊዜ ነቅታ ወደ ቅንጅታዊ አሰራር መምጣት ላይ ነች፡፡ ሁኔታውም ያስገድዳል፣ አሰራሩም ይፈቅዳል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል መርሆች መመሪያ ይሰጣሉ ይመሩናልና ለዚህ ደግሞ መታዘዝ አለብን የሚል አቋም መያዙን ገልጸዋል።
አክለውም ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ወይታ ወዛ ልማታዊ ስራዎች እና መንፈሳዊ አግልግሎቶች በአንድነት በመቀናጀት በጣም ተጠናክረው ቢቀጥሉ በሀገሪቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ትልቅ ሰራዊት ያላት ቤተክርስቲያን ነች ብለዋል፡፡















በሌላ በኩል ከተለያዩ አራት ቀጠናዎች የመጡ የቤተክርስቲያን መሪዎችና ተሳታፊዎች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ፥ በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፥ አገልግሎቱን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መምራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት መደረጉን በኮሚሽኑ የአስቾኳይ ግዜ እርዳታ እና መልሶ መቋቋም ፕሮግራም ማናጀር አቶ አብርሃም አላምቦ ተናግረዋል።
መሰል አውደ-ጥናት ከግንቦት 28/2018 ዓ.ም-ግንቦት 29/2018 የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን በአርባምንጭ ከተማ በደቡብ ምዕራብ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ማካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

Add a Comment