7G0A0211

ኮሚሽኑ የሠላም ግንባታ ስራዎችን በሰሜኑ ኢትዮጵያ እንድሰራ የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርሲቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን-የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሃይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት፡-የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሠላም ያላቸው ሚና ላይ ትኩርት ያደረገ የአቅም ግንባታ እና የምክክር ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ ሮሪ ሆቴል አካሄደ፡፡ 

በጉባኤው የተለያዮ ሃይማኖት አባቶች፣የመንግስት በለድርሻ አካላት ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣አባ ገዳዎች፣ሠላም ላይ የሚሰሩ የተለያዮ በለድርሻ አካላት፡-የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላም ያላቸው ሚና ላይ ለመምከር ተግኝተዋል፡፡ በምክክሩም በመድረኩ የተገኙ እንግዶችም ከሀላባ፣ሻሽመኔ፣ወራቤ ስልጤ ፣ሀዋሳ ዙሪያ አከባቢ፣ ከስለጤ፣ከነጌሌ አረሲ እና ከምዕራብ አርሲ የመጡ ናቸው፡፡

በምክክሩ የተገኙቱ የሃይማኖት አባቶችም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርሲቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን-የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሃይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት መሰል የሰላም ግንባታ ስራዎችን በሰሜኑ ኢትዮጵያ የአገራችን ክፍሎች እንድሰራ የሃይማኖት አባቶች ጠይቀዋል፡፡ ምክንያቱም ኮሚሽኑ በዚህ ፕሮጀክት በሰራባቸው አከባቢዎች ሠላምን፣መከባበርን በሃይማኖቶች እና በማህበርሰቡ ዘንድ ማስረጽ ችሏል ስሉ  አባቶች በጉበኤው ተናግረዋል፡፡

በኮሚሽን-የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሃይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት ማናጀር የሆኑት አቶ እንዳለ ወ/ሳማያት   የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላም ያላቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸው ነገረ ግን ሁሉም በለድርሻ አካላት ለሠላም ዘብ በመቆም እና በመጠበቅ ዘላቂ ሠላምን ማጽናት እንደሚቻል ገልጽዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ለተሳተፍዎቹ ስለ ሠላም፣መከባበር እና ግጭት አፈታት ስልጠና የሰጡት  አቶ አደነ ደቻሳ በአዲስ አበባ የሃይማኖቶች ጉባኤ/ከውንስል የሠላም ግንባታ መመሪያ ም/ኃላፊ ከተወያየን እና ከተከባበርን የማንፈተው ችግር ፡ የማንግባባበት ነገር የሌም ብለው የሃይማኖት አባቶች፣መሪዎች፣ወጣቶች፣ሴቶች፣የመንግስት በለድርሻ አካላት ሁሉ ለዘላቂ ሠላም የበኩላቸውን ድርሻ እንድወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሌላው በምክክር ጉባኤው የታደሙ ሃይማኖት አባቶች፣የመንግስት በለድርሻ አካላት ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣አባ ገዳዎች ለለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርሲቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን-የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሃይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት በተሰሩ የሠላም ግንባታ

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *