ኮሚሽኑ በጠየቅነው ጊዜ ሁሉ ድጋፍ የሚያደረግልን ትልቅ ቅን ተቋሚ ነው፡ ቂርቆስ ወረዳ

ኮሚሽኑ 1.6 ሚሊዮን ብር  የሚያወጣ የምግብ ዱቄትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማሕበረሰብ አደረገ

አድስ አበበ፡- የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን  በጠየቅነው ጊዜሁሌ አስፈላጊው ድጋፍ ለወረዳችን ማህበረሰብ የሚያደረግልን ቅን ተቋሚ ነው ስሉ በአድስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ወረዳው ሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ወ/ሮ አስተር አስራት ገለጽ፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን 1.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የምግብ ዱቄትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በጸጋ ቃ/ሕ/ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተቀናጄ የልጆች እና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት ለተመረጡ ለደሃ ደሃ የማህበርሰብ  ክፍሎች  ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ድጋፍ አደረጎል፡፡

ድጋፍ በማድረግ መረሃ ግብር ላይ የተገኘቱ የቂርቆስ ወረዳ የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አስተር አስራት ይህ ትልቅ ስራ ነው፡፡ የደሃ ደሃ  ሕጻናት እና ቤተሰብ ላይ መስራት የነጌን ትውልድ መነጽ፡ተተክ ትውልድን ማብቃት እና የደከሙትን መደገፍ ነው፡፡  

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በፀጋ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተቀናጅ የልጆች እና ወጣቶች ልማት  ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶክተር አስተር ነጋጥበብ ቤተክርስቲያኒቱ ለለፉት 28 ዓመታት በዚህ ፕሮጀክት በርካታ የደሃ ደሃ የሆኑ ልጆችን እና ቤተሰቦችን ስትደግፍ መቆየቱን ገልጽዋል፡፡  የተደረገው የድጋፍ አይነትም 25 ኪ.ግ የምግብ ዱቄት፣5 ሊትር ዛይት፣የሴቶች የንጹህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለ217 ለደሃ ደሃ ቤተሰብ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በለፉት 28 ዓመታት በተሰሩ ስራዎች በርካታ ልጆች   በተለያዮ የሙያ ዘርፍ ተሰማረተው   ለአገር እና ለቤተክርስቲያን እድገት የበኩላቸውን አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ዶክተር አስተር ነጋጥበብ በዓመት 6 ሚሊዮን ብር በመመደብ ልጆች በአምሮአዊ፣በመንፈሳዊ እና በማህበራዊ ሕወታቸው የበቁ እና ያደጉ እንድሆኑ ፕሮጀክቱ አጠንክሮ እየሰራ ነው፡፡  

የዚህ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ተገኜ ስሆን በልማት ኮሚሽኑ አመራር ሰጭነት በጸጋ ቃ/ሕ/ አጥቢያ ቤተክርስቲያን እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡

የድጋፉ ተቃሚዎችም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኞች መሆናቸውን ገልጽዋል፡፡ እንድ የድጋፍ ተጠቃሚ አባት ይህ ድርጅት ልጆቻችንን እያስተማረ፡ ስታመሙ እያሰከመ በብዙ እየደገፈን ነው፡፡ የዛሬ ድጋፍ ለእኛ ቱርጉሙ ትልቅ ነው ስሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌላኛዋ የድጋፉ ተጠቃሚ እናት በበኩላቸው ይህ ፕሮጅክት እኔንም ልጆቼንም እየደገፈ ነው፡፡ ያለ አባት ለማሳድጋቸው ልጆቼ እንደ አባት እንድሆን አቅም ሆኖኛል ብለው ይህ እንድሆነ የፈቀደ እግዚአብሔርን በቅድሚያ አመሰግናለሁ በመቀጠልም የደገፉንን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው ስሉ ደስታቸውን ገልጽዋል፡፡

በሁነቱ የታደሙ የመንግስት ኃላፊዎች ኮሚሽኑ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር የደሃ ደሃ ልጆችን እና ቤተሰብን በመረዳት በኩል እያደረገ ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ከሚሰራቸው የልማት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች ባሻገር በተለያዮ የአገርቱ ክፍሎች በሚገኙ ከ100 በሚበልጡ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት  የተቀናጅ የልጆች እና ወጣቶች ልማት  ፕሮጀክት ከፍቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

    Tags: No tags

    Add a Comment

    Your email address will not be published. Required fields are marked *