የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ሴቶችን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አመራር እና ሥነ-ስብከት ማብቃት እና ለዘላቂ ሰላም ሚናቸዉን ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ የስልጠና እና የዉይይት መድረክ በሐዋሳ ታቦር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ከየካቲት 26-30/2017 ዓ.ም አካሄደ፡፡
ስልጠነውም በኮሚሽኑ ሰላም ግንባታ እና ስርዓት ጾታ ፕሮግራም/ የጂስራ ፕሮጀክት የተዘጋጀ ሲሆን ከወራቤ፣ስልጤ ፣ሻሽመኔ፣ነጌሌ እና ሐዋሳ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሕብርት እና ቀጠና የተገኙ ሴት እህቶች እና እናቶች ስልጠናውን ተከታትለዋል፡፡


ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት የሴቶች አገልግሎት መምሪያ ወ/ሮ ብዙነሽ ጡምስዶ እና በላይነሽ ላቀው ከሕይወት ልምድ እና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር በግጭት አፈታት፣ የስነ-ስብከት እና ሰላም ግንባታ ላይ ስልጠና ሰተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት የሴቶች አገልግሎት መምሪያ አስተባባሪ ወ/ሮ ብዙነሽ ጡምስዶ ቤተክርስቲያኒቱ ከልማት ኮሚሽኑ ጄስራ ፕሮጀክት ጋር በመሆን ሴቶችን በሥነ ስብከት ማብቃት እና ለዘላቅ ሰላም የበኩላቸውን ሚና እንድጫወቱ በማድረግ ረገድ ላለፉት 5 ዓመታት የተለያዮ ተግባራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጥ መቆየቱን ገልጽ ሴቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ማብቃት እና የሰላም መሳሪያ መድረግ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን አንዱ የእስትራቴጂክ/ስልታዊ ዕቅድ አካል ነው ብላለች፡፡


















ትኩረት አረገን እየሰራን ያለነው አከባቢዎች ማለትም ከወራቤ፣ስልጤ ፣ሻሽመኔ፣ነጌሌ እና ሐዋሳ ማዕከል ያደረገ ነው፡፡ በዝህ አከባቢ ደግሞ የቤተክርስቲያን ስደት እና የተለያዮ ግጭቶች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች የሚቸገሩበት ቦታ ነው፡፡ ሀላባ፣ስራሮ፣ወራቤ ላይ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎብናል፡፡ ነገር ግን እኛ የሠላም ሰዎች ነን፡፡ ወንጌላችንም የሠላም ወንጌል ነው፡፡ ለዚህ ነው ከሌሎች የኃይማኖት አባቶች እና እናቶችም ጋር በመሆን ሠላምን ለማምጣት እና ለማጽናት እየተጋን ያለነው፡፡
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት የሴቶች አገልግሎት መምሪያ ረዳት አስተባባሪ ወ/ሮ በላይነሽ ላቀው ሴቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ኑሮኦቸው፡ የስብከት ዘዴ፣የማስተማር ዘዴ እና እንዲሁም የግጭት ምንነት እና አፍታት ላይ ለተከታታይ አምስት ዓመታት ት/ት እና ስልጠና ወስደዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ግጭቶችን ማስወገድ እና ማስቀረት ችለናል ስትል ገልዋል፡፡
በቤተክርስቲያን፣በቤተሰብ፣በቤተ-እምነቶች እና በአገር ደረጃ የሚከሰቱ ችግሮችን እና ግጭቶችን ማጥበብ ተችሎል ያሉት ወ/ሮ ባላይነሽ፡፡ ሰልጣኞቹ በጣም ግጭቶች ከሉበት አከባቢ የመጡ ሲሆን ስለ ግጭት ምንነት እና አፍታት ከስልጣነው በገኙት እውቀት እና ልምድ በየአከባቢያቸው በጽሎትም ሆነ ግጭትን በመፍታትን ግጭቶች እንድቀንስ መስራት መቻለቸውን አድንቀው ስልጠናወን ለተከታተሉትም የሰረትፍኬት እና የዕውቅና ተሰጥቶቸዋል፡፡
ከማሃል ደቡብ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በስልጠናው የተገኙት ወንጌላዊት ወ/ሮ ማስተወት ማሞ በቀጠናው የሴቶች አገልግሎት አስተባባሪ በበኩላቸው ስልጠናው በጣም ጠቃሚ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡ ከስልጠናው ያገኜሁትን ት/ት እና ልምድ በ16 የቤተክርስቲያኒቱ ሕብረቶች ማካፈላቸውን ገልጽው የተጣሉ በለትዳሮችን ማስታረቅ እና ትደራ እንዳይፈረስ ማድረግ መቻላቸውን ተናግረው እግዝአብሔርን አመስግነዋል፡፡ ለሠላም እና ግጭት መፍታትን በዘላቅነት ስራችን አድረግን እንቀጥላለን እግዝአብሔረም ይረደናል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ የመንዝወረቅ ተምሩ ከስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የመጣቸው ሌላኛው የሰልጣናው ተሳታፊ ስትሆን ከስልጣነው በፍት ስለ ግጭት አፈታት እና ምንነት በጋራ ሆነ በግል በቂ ግንዛቤ እንዳልነበራት ገልጻ ከስልጣናው ቦሆላ ስለ ግጭት አፈታት ጥሩ መረዳት፣እውቀት እና ልምድ እንደገኘች ተናግራለች፡፡
ሌላኛዋ ወ/ሮ የመንዝወረቅ ሀሳብ የተጋሩት ውንጌላዊት ብርቅነሽ ተደሰ ከሀላባ ዞን እና ዙሪያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሴቶች አገልግሎት አስተባባሪ እና ጽሐፍ ስልጣነው የሚፈጠሩ ዘረፈ ዘርፈ ብዙ ግጭቶችን እንደት መፈታት እንደሚንችል አድረጎናል፡፡ የአምስት ዓመታት ጉዞአችንም ስኬታማ ነው ስትል ገልጻለች፡፡




ከምዕራብ አርሲ ልዮ ሕብርት የሴቶች አገልግሎት ሰብሳብ የሆኑት ወ/ሮ ታረኬ ተስማ ከመሰልጠናችን በለፈ እግዙአብሔር ብዙ ስራ ስሰራ አይተናል፡፡ ከእኛ አልፈን ለሌሎች ሠላም መስራት እንድንችል አስችሎናል፡፡ ሙስልሙ፣ኦረቶዶክሱ እና ሌሎችም እንዴት በሠላም ለሠላም መስራት እንዳለብን ግንዛቤያችንን አሳድጎል፡፡

በልማት ኮሚሽኑ የጄንደር በለሙያ ወ/ሮ ተመነች ዮሴፍ በበኩላ ልማት ኮሚሽኑ ከምን ግዜው በላይ ሴቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ለማብቃት እየሰራ እንደምገኝ የገለጽች ስሆን ያለ መተከት ስልጠነው ለለፉት አምስት ዓመታት ኮሚሽኑ በሚያዘጋጀው መድረክ ሁሉ በመገኜት ለሰለጠኑ ሁሉ አድናቆቶን ገልጻ ከስልጣነው ያገኛቸሁት ዕውቀት እና ልምድ ለሁለንተናዊ እና ዘላቅ ሠላም በቀጣይነት እንድትሰሩ ስትል ለተሳታፊዎች መልዕክት አስተላልፋለች፡፡

እንዲሁም በልማት ኮሚሽኑ የጄስራ ፕሮጀክት ማናጀር የሆኑት አቶ እንዳለ ወ/ሳማያት በዋናነት ይህ ፕሮጀክት ግጭትን በመከላከል፣ ግጭትን ወደ ጋራ ጥቅም በመቀየር ላይ ነው የሚሰራው፡፡ እኛ ደግም የሳላም አምባሳደሮች ነን፡፡ ስለዝህ ላሌሎች ሠላም እንሰራለን፡ ፡እንተጋለን፡፡ ሠላምን እናጽናለን ስል ገልጾል፡፡

Add a Comment