የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በደቡብ ኦሞ እና ቦረና በድርቅና ጎርፍ አደጋ የተጎዱ ከ38 ሺህ በላይ ሰዎችን በአስቾኮይ ጊዜ የሚግብ ሥርጭት እረዳታ ፕሮጀክት በቦረና ዞን ተልተሌ አከባቢ እና በደቡብ ኦሞ ዞን በሀመረ እና ባና-ፀማይ አከባቢ ተጠቃሚ ማድረጉ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸውም በፕሮጀክቱ መዝግያ ፕሮግራም ሀምሌ 11/2016 ዓ.ም በደቡብ ኦሞ ዞን ደመካ ከተማ በተደረገ ፕሮግራም ነው፡፡ በፕሮግራሙ በልማት ኮሚሽኑ አስተኳይ ዕርዳታ እና መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮግራም ማናጀር የሆኑት አቶ አብረሃም አለምቦ የፕሮጀክቱን አፈጻጻም ሪፓርት አቅረበዋል ፡፡ ባቀረቡበትም ወቅት ይህ ፕሮጀክት በኮምፓሽን ኢንተርናሽናል የታገዘ እና በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን የተሰራ መሆኑ እና 38,754 በድረቅ እና በጎርፍ አደጋ የተጉዱ ማህበረሰቦችን ኮሚሽኑ በሰራው ስራ ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ ድርስ የተሰራ ሲሆን ለእያንዳንዱ ተጠቃሚዎቹ 15 ክ.ግ የቦቆሎ ዱቄት፣0.5 ሊትር ዘይት፣1.5 ክ.ግ ቦሌቄ፣ CSB/famix 4.5 ለሁለት ወራት ስርጭት ተደረጎል ያሉት አቶ አብረሃም የፕሮጀክቱ አጠቃለይ በጀት 94.2 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን ገጸዋል፡፡


አቶ መዕከል ማሊኮ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳር በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት በዋናነት የአከባቢው መንግስት ሊመልስ ያልቻለውን የህዝባችንን ችግር የፈታ ፕሮጀክት ነው ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በድርቅ እና በጎረፍ አደጋ የተጉዱና የተራቡ ህዝባችንን አብልቶል፡፡ የወደቀን እንስቶ የማይረሳ አሻራ አስቀምጦል ምክንያቱም ህዝባችን በረሃብ ከመሞት አድኖል፡፡ በብዙ ማስዋዕትነት ህዝባችንን ከድርቅ እና ከጎርፍ አደጋ ታድጋቹሁታል ያሉ ሲሆን አክለዉም በህዝባችን እና በዞኑ አስተዳደር ስም ልማት ኮሚሽኑን እና ኮምፓሽን ኢንተርናሽናልን ከልብ እናመሰግናለን ያሉት አስተዳዳሪዉ የኢትዮጽያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ስራ ለሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም ምሳሌ የሚሆን ስራ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ኦም የጤና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታምራት አሰፋ በበኩሉ ከልማት ኮሚሽኑ የአስቾኮይ ምግብ እርዳታ በፊት የነፈሰ ጡር ሴቶች፣የአጥቢ እናቶች፣ የህጻናት እና ሽማግሌዎች ህይወት እና ጤና አደጋ ላይ ነበረ፡፡ አሁን ግን በተደረገላቸው የምግብ እርዳታ አመጋገባቸው መስተካከሉን በየሳምንቱ ከየጤና ማዕከሉ በምንሰበስበው መረጃ መረዳት ችለናል፡፡ ይህ የሆነው በልማት ኮሚሽኑ እርዳታ መሆኑን አቶ ታምራት ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ከፍተኛ የክልል፣የዞን እና የፌደራል መንግስት አካለት የተገኙበት ፕሮግራም ሲሆን ከፌደራል አደጋ ስጋት መከላከል ኮሚሽን የተገኙት እንግዶችም የመስክ ምልከታ ጭምር በማድረግ ተጠቃሚዎችን መነጋገረ ችለዋል፡፡

በመስክ ምልከታም በፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የአጋር አካላት ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ፈቃዱ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በደቡብ ኦሞ ዞን እና ቦረና ዞን ያደረገውን የአስቾኮይ የምግብ እና ምግብ ነክ እርዳታን አድነቀው፡ልማት ኮሚሽኑም መሰል የእረዳታ ስራዎችን በአከባቢው ቢቀጥል የበለጥ ማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ይኖረዋል ሲሉ ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜናም ወ/ሪት ማሚቱ አበራ ከፌደራል አደጋ ስጋት አመራር አመራር ኮሚሽን የፕሮጀክት ግምገማ ከፍተኛ በለሙያ የተደረገው ድጋፍ መልካም እና የተጎጂ ማህበረሰብን ፈላጎት ቀዳሚ ያደረገ በመሆኑ ልማት ኮሚሽኑን የሚያስመሰግን ስራ መስራቱን እና በመስክ ምልከታም ከተጠቃሚዎች ጋር በነበራት ቆይታ እንደረጋገጠች ገልጻለች፡፡

አቶ ማሞ ሞሊሶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የሲቨል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጉዳይ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩሉ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን የአስቾኮይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ስርጭት ሁሉም በለድርሻ አካላት በተገኙበት የተደረገ እና ውጤታማ ስራ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡ ልማት ኮሚሽኑ እና የሚመለከታቸው አካላት በጋራ መስራት በመቻለቸው ስራው በስኬት የተፈለገውን አላማ ማሳካቱን አቶ ማሞ ተናግረዋል፡፡
የተጠቃሚዎችን እና ሌሎች ምስክርነቶችን በቅረቡ እናጋራቹሃለን ማህበራዊ ገጾቻችን በመከታተል መረጃዎቻችንን ያግኙ::

Add a Comment