




የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን በ700 ሺህ ዶላር በጦርነት ለተጎዱ ሰዎች የአስቾኮይ ጊዜ እርዳታ እና መልሶ የመቋቋም ስራ አላማጣን ጨምሮ በ5 ወረዳዎች በ21 ቀበሌዎች 4500 ቤተሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደረግ ቅደም ማገገም የግብርና ፕሮጀክት ስራ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡
ይህ ፕሮጀክት በአላማጣ ከተማ፣ራያ አላማጣ፣ኮርም፣ኦፉላ፣ጨርጭር እና ዛታ ወረዳዎች በ21 ቀበሌዎች 4500 ቤተሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደረግ ስሆን በጦርነት የተጉዳውን የማህበረሰቡን የግብርና እና የማህበረሰብ ኑሮን በማሻሻል እና በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጨወተ ይገኛል፡፡







ፕሮጀክቱም 50 ክሎ ግራም መዳበሪያ፣12.5 ክሎ ግራም ጤፍ፣10 ክሎ ግራም ማሽላ፣ የግብርና መሳሪያዎች እና ሌሎች መሰል ድጋፎችን ለደሃ ደሃ ለሆኑ፣በጦረነት ለተጎዱ እና ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ማድረጉን አቶ ኤፍሬም ከበዴ በኮሚሽኑ የአስቾኮይ ጊዜ እርዳታ እና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም አስተባባሪ ገልጸዋል፡፡
አክለውም አቶ ኤፍሬም ከበደ ይህም ፕሮጀክት ተጠቃሚዎችን ከመደገፍ ባሻገር በዘላቂነት የምግብ ዋስትና እንዲያረጋግጡ እና የዕለት ገቢያቸውን እንድያሳድጉ ያግዛቸዋል ብለው አከባቢው በጦርነት የተጎዳ በመሆኑ ሁሉን ለመድርስ ይህ ድጋፍ በቂ ነው በይባልም ነገረ ግን ድጋፍ የተደረገላቸው ቤተሰቦች ኑሮ መልሶ ከመገንባት አንጻር ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

በራያ አላማጣ ወረዳ የሁልግዜለምለም ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ፀጋ አብረሀ የ4 ልጆች እናት ሰሆን ኮሚሽኑ 12.5 ከ.ግ የጤፍ ዘር እና 50ከ.ግ መዳበሪያ ድጋፍ እንደሰጣቸው ይናገራል፡፡
አክለውም የጤፍ ዘርን እና መዳበሪያን ከገበያ ገዝተን ለመዝራት አቅማችን አይችልም ያሉት ወ/ሮ ፀጋ አብረሀ የተደረገልን ድጋፍ እርሻችንን በዘር እንድንሸፍን እንደገዛቸው ገልጸው ይህም ይህ ድጋፍ የወደፊት የምግብ ዋስትናችንን እውን ለማድረግ ቁልፍ ተስፋ መሆኑን አመላክተዋል። ኮሚሽኑ ለሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አቅመ ደካሞች እያደረገ ያለውን የድጋፍ ስራም አድንቀዋል።

ሌላኛው የአላማጣ ወረዳ ገርጃሌ ወረዳ ነዋሪ አማረ ሳሌ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆነ አካል ጉዳተኛ እና የሰባት ልጆች አባት ነው። በአካባቢው የተካሄደው ጦርነት የእያንዳንዱን ግለሰብ ህይወት እንደጉዳቸው ገልጸው የዚህ ፕሮጀክት ድጋፍ ለተጎዳው ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ በተለይ ለገበሬዎች የዚህ ፕሮጀክት ትርጉም በቃል ከመግለጽ የላቀ ነው። ጠቃሚ ድጋፍ ነው የተሰጠን ያሉት አቶ አማር በፕሮጀክቱ 12.5 ኪሎ ግራም የጤፍ ዘር እና 5 ፍየሎች ማለትም ሁለት ወንድ እና 3 ሴት ፍየሎችን ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል ።

እርሻዬ በጤፍ መሸፈን ቻልኩ፡፡ የጤፍ አዝማራው ያማር ነው፡፡ ጥሩ ምርት እጠብቃለው፡፡ አንድ ፍየል እርጉዝ ነች፡፡ በቅርቡ ትወልዳለች፡፡ ፍየሎችን በመራባት እና በከብት / በላሞች ለመተካት እቅድ አለኝ፡፡ ኮሚሽኑን ለደረገልን ድጋፍ እኔን እና ቤተሰቦቼ ከልብ እናመሰግናለን ።



ሌሎችም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች የተደረገላቸው ድጋፍ በጦረነት የተጎዳውን ኑሮ በማሻሻል ረገድ ድጋፍ ላቅ ያለ ሚና እንደለው ገልጸው እናት እና አበት እንኳን በዚህ ጊዜ የማያደረጉትን አይነት ድጋፍ ነው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ያደረገልን ስል ልባዊ ምስጋናቸውን አቅረበዋል፡፡










በአጠቃላይ ይህ ፕሮጀክት ለአባወራዎቹ ግማሽ ሄክታር መሬት ለመሸፈን የሚያስችል የተሻሻለ ዘር (ጤፍ 12.5 ኪሎ ግራም እና ማሽላ፡ 10 ኪሎ ግራም ) ፣ የግብርና መረጃ መሳሪያዎች 4,500 አባ ወራ እና እማ ወራ፣ የማዳበሪያ ድጋፍ 1,357 አባ ወራ እና እማ ወራ፣ የጓሮ አትክልት ዘር ለ25 ታጠቃሚዎች ድጋፍ የተደረገ ስሆን ይህ በአከባቢው በነበር ግጭት/ጠርነት የተጎዳውን የማህበረሰቡን የምግብ ዋስትና፣ ኑሮ እና የቤተሰብ ገቢ በማሻሻል ርገድ ቁልፍ አለው።
Add a Comment