662477926_919419134203956_4739452365985795650_n

“ቃለ ሕይወት ጅራ፣ ብሻን ጅራ/ ቃለ ሕይወት በለበት ውሀ አለ” አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ የቤተክርስቲያኒቱ ም/ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ

“ቃለ ሕይወት ጅራ፣ ብሻን ጅራ/ ቃለ ሕይወት በለበት ውሀ አለ” አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ የቤተክርስቲያኒቱ ም/ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀራርጌ ሚደጋቶላ ወረዳ ያስቆፈርውን የንጹሁ መጠጥ ዉሀ የፌድራል፣የክልል፣የዞን እና የወረዳ እንዲሁም አጋር አካላት በተገኙበት መጋቢት22/2018ዓ.ም በደማቅ አስመረቋል፡፡

ይህ ለምረቃው የበቃው የመጠጥ ውሀ ጉድጓድ ከ280 ሜትር ባላይ ጥልቀት ያለው የንጹሁ መጠጥ ዉሀ ጉድጓድ ስሆን በኡርጂ እና ሌንጫ ቀበሌ የሚገኙ 300 ቤተሰብ ወይም 18 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ነው፡፡

ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ውጭ የተደረገበት ይህ የመጠጥ ዉሀ ጉድጓድ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም በይፋ ተመረቋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያ ም/ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ በምርቃቱ ፕሮግራም በመገኜት “ቃለ ሕይወት በለበት ውሀ አለ/ቃለ ሕይወት ጅራ ብሻን ጅራ” በማለት በፕሮግራሙ ለተገኙ የአከባቢው ማህበረሰብ እና እንግዶች እንኳን ደስ አላቹሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቤተክርስቲያኒቱ ከወንጌል አገልግሎት ባሻገር የልማት ስራዎችም እ.ኤ.አ ከ1928 ጀምሮ የልማት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን እሰራች ያለች ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ከ10ሺህ በላይ አጥቢያ ቤተክርስቲያ እና ከ12 ሚልዮን ባላይ ተከታይ ምዕመናን ያሏት ስሆን በኮሚሽኑ በኩል በዉሀ፣ በጤና፣ የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻል፣ የራስ አገዝ ቡድን ማደራጀት፣ በአስቾኳይ ጊዜ እርዳታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን በሰፊው እየሰራች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ይህ የመጠጥ ዉሀ ጉድጓድ ከዕቅድ ጀምሮ በብዙ መንገድ ዘሬ ላይ እውን እንድሆን የበኩላቸውን ድርሻ ላደረጉ ለመንግስት፣ ለበጎ አድራጎት ድርጂቶች እና በለድርሻ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ስሆን ለማህበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ያደረገውን ደች ሪሊፍ አሊያንስ አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተፈራ ተሎሬ(ደ/ር) በሚረቀው ስነ ስርዓት ላይ ዛሬ የተለች ቀን ናት፡ ለዚህ ማህበረሰብ የንጹሁ የመጠጥ ዉሀ ለመቆፈር የመሰረተ ድንጋይ ያስቀመጥነውን የዛሬ ዓመት ነበር፡፡ በብዙ ልፋት እና ጥረት ዛሬ ይህን ዕቅድ አሳክተን ዛሬ እያስመረቅን ነው፡፡ ማህበረሰቡም ንጹሁ የመጠጥ ውሀ በአቅራቢያው አግኝቷል፡፡ ኮሚሽኑም ዕቅዱን አሳክቷል፡፡ እንኳን ደስ አላቹሁ በማለት ይህን ዉሀ በአግባቡ እና በኃላፊነት በመጠቀም ሁለንተናዊ ለውጥ በጤና፣በትምህርት ልማትና ዕድገት ማምጣት እንዲችሉ ጥሪ አድረገዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶም ብራቱ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን፣ቲረፈንድና ኤስኦኤሰ በዚህ አከባቢ ዘርፈ ብዙ የልማት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን ሰረቷል፡፡ እሰከዛሬ ለስራቹሁት ስራ፡ ህዝቡ ህዝባችን ነው ብላቹሁ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የስራችሁት ስራ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም አቶ ሳምሶም ብራቱ የሚታይ የሚጨበጥ ስራ በመሰራቱ እና የህብርተሰቡን ዘረፍ ብዙ ችግሮችን ስራ በመሆኑ በስራው በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ የድርሻቸውን ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ጋር የተባበራቹሁ አጋር አካለት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በለስልጣን ስም የምስጋና መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የተሰራወ ስራ ከሚታሰበው በላይ ነው ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶም ብራቱ ይህን መሰል የልማት ስራዎች ሳይቋረጡ በጣም በላቀ መልኩ ማስቀጠል ያስፈልጋል ስሉ መልዕክታቸውን ለበለድርሻ አካላት ገልጸዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *