
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች እና ለኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ወጣቶች በዘላቂ ሠላም ግንባታ ዘርፍ የወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጥ እና የምክክር ስልጠና መድረክ በሀዋሳ ከተማ ከ21/11/2017-23/11/2017 ዓ.ም አካሄደ፡፡

ከሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀን ስሰጥ የነበረው የወጣቶችን ተሳትፎ ለዘላቂ ሠላም ግንበታ ላይ ትኩረት ያደረገው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡

በስልጣናውም 60 ሰልጣኞች የተገኙ ስሆኑ የመጡትም ሰልጣኞች ከሆሳና፣ከሀላባ፣ወራቤ፣ሻሽመኔ፣ከወላይታ ሶዶ፣ከሀዋሳ/ስዳማ እና አረባምንጭ አከባቢ ከሚገኙ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያናት እና ከቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ነው፡፡



ስለ ግጭት አፈታት እና ሠላም ግንባታ እና የተለያዮ የሠላም ጉዳዮችን በተመለከተ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ለ60 ወጣቶች ስልጣና ተሰጥቷል፡፡ ወጣቶች በመንፈሳዊ እና በሠላም ግንበታ ዘረፍ ያለቸውን ሚና በማንሳት ይህን ዓለም እንዳያሸንፋቸው በእግዚአብሔር ቃል እውነት መሞላት እና መታጠቅ እንደሚያስፈልግ የገለጹት በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሀገር አቀፍ የዮንቨርስቲ ተማሪዎች እና የወጣቶች አገልግሎት አስተባበሪ ወንጌላዊ ያቆብ በዛብህ ናቸው፡፡

ያለፉት አምስት ዓመታት የኮሚሽኑ ጄስራ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ዘርፍ ጋር በሰራቸው የሠላም ግንባታ ስራዎች የሃይማኖት ግጭቶች፣ስደቶች በመጠኑም ቢሆን የመቀነስ ሁኔታ አሳይቷል ያሉት ወንጌላዊ ያዕቆብ በሃይማኖቶች መካካል የመከባበር በህል እንድዳብር እያደረገ ያለውን የፕሮጀክቱን ድጋፍ እና እንቅስቃሴን አድንቀዋል፡፡
አክለውም ውንጌላዉ ያዕቆብ በዛብህ ወጣቶች በእግዚአብሔርን ቃል እውነት እና ጸሎት መንፈሳቸውን፣ስጋቸውን እና ነፍሳቸወን በመደገፍ ስሜታውነትን በመቆጣጠረ፣ ክፉ ከሆኑ ከስጋዊ ምኞቶች በመተው ወጣቶች በመንፈሳዊ እና በማህበራዊ ሕይወታቸው እግዚአብሔርን አክብረው እና በማህበረሰቡ ዘንድ በጎ ተጽዕኖ ማሳደረ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የትኛውም አይነት አውደም ግጭት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አላማውን ለማሳከት ከፍተኛ የሆነ የወጣቶችን ተሳትፎ ይፈልጋል፡፡ይህም ተሳትፎ አካላዊ መጉደለን ጨምሮ ነፍስ እስከ መሰዋት ሊያደረስ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወጣቶች የግጭትን አስከፊነት በማወቅ ከግጭት ይልቅ ለሠላም እንድሰሩ በኮሚሽኑ የጄስራ ፕሮጀክት ኃላፊ/ማናጀረ አቶ እንደለ ወ/ሳማያት መክረዋል፡፡ ይህም እንደ ግለሰብ እና እንደ ማህበረሰብ ሁሉም ሊያደብረው የሚገባ የዘላቅ ሠላም ግንባታ አዋጪ ሠላማዊ መንገድ ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት በሰራቸው የሠላም ግንባታ ስራዎች በርካታ ተስፋ ሰጭ ነገሮችን ማየት ችለናል፡፡ በሃይማኖች ዘንድ የመቀራረብ እና የመከባበር በህል እያደገ ነው፡፡ ነገረ ግን ይህ መልካም በጀምር ያሉ ጠቃሚ የጋራ እሴቶች ናቸው፡፡ ፕሮጀክቱ ግዜውን ብጨረስም ማህበረሰቡ እና ወጣቶቹ የማስቀጠል የጋራ ኃላፍነት አለበቹሁ ስሉ ለሰልጣኖች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በስልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም ከስልጠናው ጠቃም ልምድ መቅሰማቸውን ገልጸው ስልጠናው እንዴት ከሌሎች ኃይማኖቶች እና ማህበረሰብ ጋር በሠላም ተከባብረን መኖር እንደለብን አቅጣጫ ያሳየ እና ጠቃም ልምድ ያገኘንበት ነው፡፡
አቶ ደስታ ሔላሎ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኮሚሽኑ የጄስራ ፕሮጀክት አስተባበሪ በበኩሉ በተሰሩ ስራዎች ዘርፈ ብዙ ስጋቶችን መቀነስ መቻሉን ገልጾል፡፡ በሃይማኖቶች ዘንድ መቀራረብ ተፈጥሮል፡፡ ለሠላም አብሮ መወገን እና የመስራት ልምድ ዳብሯል ነገረ ግን ጠንክሮ እንድቀጥል የሁሉም በለድርሻ አካላት ክትትል እና ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል፡፡

Add a Comment