
ቢሾፍቱ፡-መስከረም 11/2019 እስከ መስከረም 13/2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የአካታች ትምህርት ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በሶስት ወረዳዎች የትምህርት ቁሳቁስ ስርጭት አደረገ፡፡
ደብተር፣አስክብሪቶ፣የትምህርት ቤት ቦርሳና ሌሎች ቁሳቁሶች ስርጭት በሶስት ወረዳዎች ማለትም በአዳአ፣ በጊምብቹና በሉሜ ወረዳ መደረጉን በኮሚሽኑ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ተሾመ ደረሰ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሲዮ ፋውንዴሽን ገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን እየተሰራ ያለና ለብዙ አከል ጉደተኞች እና ቤተሰብ ተስፋ የሆነ ፕሮጀክት ነው፡፡
እንደሚታወቀው መስከረም ወር በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ ከመሆኑ አንጻር ፕሮጀክቱ የደብተር፣ የተለያዩ ስቴሽነሪዎችን፣ እስክሪቢቶ፣ ቦርሳ ግብዓቶችን አካል ጉዳተኛ እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እያቀረበ ይገኛል። በዚህ ዓመት ለሶስቱ ወረዳዎች እስከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚደርስ የደብተር፣ ቦርሳ፣ መማሪያ ቁሳቁሶችን በመግዛት ለተማሪዎች ስርጭት ተደረጎል።














በተስራው የማህበረሰብ አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻና የአቅም ግንባታ ስልጣናዎች ይህ የአካታች ትምህርት ፕሮጀክት አካል ጉዳተኛ ልጆች አካል ጉዳተኝነት እንቅፋት ሳይሆንባቸው ትምህርት መማር እንድችሉ እያደረግ ይገኛል፡፡ ለአካል ጉዳተኞችም እንደየጉዳታቸው ማለትም የአይን ቀዶጥገና ህክምና፣የአካል ድጋፍ መርጃ መሳሪያ፣የምግብ አቅረቦት፣ ቤተሰቦቻቸውን ደግሞ በራስ አገዝ ቡድን ማደራጀት እና ቁጠባ እንድጀምሩ በማድረግ ሰፊ የድጋፍ ስራዎች መደረጉን አስተባበሪው ተናግረዋል፡፡







ከቁሳቁስ እጥረት የተነሳ ከትምህርት ገበታ የሚቀሩ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ እንድመለሱ ከማድረግ አንጻር ከፍታኛ አስተዋጾ እንዳለው የተናገሩ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ በሶስት ወረዳዎች በ30 ትምህርት ቤቶች የአካታች ትምህርት እንድጠናከረ ከማድረግ አንጻር አይነተኛ ሚና እየተጨወተ እንዳለ ተገልጾል፡፡
በተጨማሪም ትምህርት ቤቶች ውስጥ መምህራን ሊረዱ የሚችሉ እንደ ፐዝሎች መገዛቱን የገልጹ ሲሆን ለተማሪዎችና ለመምህራን መልካም የመማር እና ማስተማር ዘመን እንዲሆንላቸው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ተመኝተዋል።
የተደረገላቸው ድጋፍ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካለ ምንም ችግር እንዲማሩና እንዲበረታቱ ትልቅ የሆነ የሞራል ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም የወላጆችንም ሸክም በመጋራት ልጆች በትምህርት ገበታ ላይ እንድገኙ ትልቅ እድል ፕሮጀክቱ መፍጠሩን ግንዛቤ ተወስዶል።
በፕሮጀክቱ 192 ወላጆች በ17 የራስ አገዝ ቡድኖች የተደራጁ ሲሆን የስምንት ወር ቁጠባቸው ከተሰጣቸው መነሻ ከፕታል ከ120ሺህ ብር ውጭ ወደ ግማሽ ሚሊዮን እንደተጠጋ ተገልጾል፡፡ የራስ አገዝ ቡድን አባላትም ከቡድናቸው ብድር በመውሰድ የተለያዮ የንግድ ስራ ላይ መሰማረታቸው ተገልጾል፡፡










ኤረገቾ በላይ የግንብቹ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት/ቤት ሰራተኛ እና የፕሮጀክቱ የመንግስት ተወካይ በበኩሉ ቃለ ሕይወት ለወረዳችን ብዙ ስራ ሰርቶልናል። በተለይ አካል ጉዳት ያላቸው ልጆችን ከቤት ፈልጎ እያወጣ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ በጣም ብዙ ስራ ሰርቷል። ለአስተማሪዎችም እንዴት አካል ጉደተኛ ልጆችን መገዝ እና ማስተማረ እንደለባቸው ብዙ ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡






የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችም ፕሮጀክቱ ለልጆቻቸው ሁለንተናዊ ለውጥ እያደረገ ስላለው ድጋፍ የላቀ ምስጋና አቅረበዋል፡፡

Add a Comment