አርባምንጭ፡– የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ልማትና ሰብዓዊ ሥራዎችን ከቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ አገልግሎት ጋር አቀናጅቶ ለማስኬድ የሚረዳ አወደ-ጥናት በአርባምንጭ ከተማ በደቡብ ምዕራብ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ግንቦት 28/2018 ዓ.ም-ግንቦት 29/2018 አካሄደ፡፡
በአወደ-ጥናቱ የተገኘቱ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ ቦርድ ሰብሳብ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ ከተለያዮ 4 ቀጠናዎች በአውደ-ጥናቱ ለተደሙ መሪዎች የእንኳን ደህና መጣቹ መልዕክት በማስተላለፍ እና ስለ አውደ ጥናቱ ዓላማ ገለጻ በማድረግ ሙሉ ወንጌል ለሙሉ ሰው በሚል የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል፡፡











አውደ-ጥናቱ የወንጌልና የልማት አገልግሎቶችን የሚያቀናጅ ታሪካዊ የምክክር መድረክ እንደሆነ የገለጹት አቶ ዳንኤል በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የተለያዩ ቀጠናዎች የተውጣጡ መሪዎችና ባለድርሻ አካላት በጋራ መሳተፋቸወን አድንቀው። ይህም በደቡብ ምዕራብ ቀጠና ቅንጅታው አሰራር መተግበር መጀመሩን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
በመድረኩም “ሙሉ ወንጌል ለሙሉ ሰው” በሚል ርዕስ ስለ ቅንጅታዊ አሰራር አላማ ሰፋ ያለ ገለጻ ያደረጉት የቤተክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ ቦርድ ሳብሳብ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ ቤተክርስቲያኒቱ ከተመሰረተችበት ከ1920ዎቹ ጀምሮ ልማትንና ወንጌልን ጎን ለጎን በማስኬድ አካላዊ፣ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ትልቅ አሻራ አሳርፋለች። ሆኖም ግን፣ በሂደት የልማት ስራዎች ይበልጥ ዘመናዊና በፕሮጀክት መልክ መዋቀር ከጀመሩ ወዲህ፣ በሁለቱ ዘርፎች መካከል የተወሰነ የመለያየት ክፍተት መፈጠሩ ተገልጿል።







በቅንጅት መስራትና ሀብት ማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት አቶ ዳንኤል ከለጋሾች ብቻ በሚደረግ ድጋፍ መጓዝ መቅረት አለበት፣በአከባቢ ሀብት እና አቅም ላይ የተመሰረተ ልማት፣በትስስት ግንኙነት ላይ የተመሰረተ የወንጌል ስራ፣ተጠያቂነት ያለው የአስተዳደር አደረጃጅትና ተቋማዊ ትስስር በቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ አገልግሎትና የልማትና ሰብዓዊ ስራዎችከምንም ጊዜም በላይ ይበልጥ መጠንከር እና መጎልበት አለበት ብለዋል፡፡
እግዚአብሔር ያልሰጠንን ድህነት ሰርተን መሸነፍ፡ያለንን ሀብት ማልማት ያስፈልጋል፡፡ አባቶቻችን ግንባራቸውን ለውንጌል እውነት ሰጠዋል፡፡ በዚህ ዘመን ያለን እኛ ለስም እና ለዝና ብለን የወንጌል እውነት መሸፈን የለብንም፡፡ ቤተክርስቲያናችን ስትመሰረት አሳተፍ የሆነ የልማት ስርዓት ነው ያላት፡፡ አሁንም ወደ ቀደመው የወንጌል ስራ እና ልማት መመለስ፡ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ቦርድ ሰፊ ስራ እየሰራ ሲሆን፥ ቤተክርስቲያኒቱ መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ ችግሩን በሚፈታ መልኩ፣ ከቃለ ሕይወት አልፎ እንደ አገር ትልቅ ለውጥ በሚያመጣ አቋም ላይ ከፍተኛና ሰፊ ዕቅድ አውጥታ እየሰራች ሆኑን የልማት ኮሚሽኑ ቦርድ አባልና የደቡብ ምዕራብ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተክረስቲያን ምክትል ሳብሳቢ አቶ ዳዊት ደጉ ተናግረዋል። አክለውም እግዚአብሔር በእያንዳንዱ አጥቢያ፣ ህብረትና ቀጠናዎች ውስጥ ትልቅ ጸጋ የሰጠ በመሆኑ፥ ከውጪ የሚመጣውን እርዳታ ከመጠበቅ ይልቅ በአካባቢያችን ያለውን ሀብት በጥራት ጥቅም ላይ ማዋልና ክፍተቶችን መልሶ ማየት እንደሚገባ ተገልጿል። በአካባቢያችን ያሉትን ሀብቶች በመጠቀም የወንጌልና የልማት ስራዎችን አቀናጅቶ፥ በትክክል ለውጥ ሊያመጣ በሚችል አቅጣጫ መስራት እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል። ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በየትኛውም አቅጣጫ የሚገኘው ህዝቧ ይህንን ሃሳብ ተቀብሎ፥ እጅ ለእጅ ተያይዞ፣ ሀብትንና የሰውን ኃይል በማቀናጀት ቤተክርስቲያንን ማሻገርና ለውጥ ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ተሎሬ ኮሚሽኑ የ10 ዓመት ስልታዊ አቅጣጫ እና የ5 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ በማዘጋጀት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር እና ሀብት መሰባሰቢያ ማኖል በማዘጋጀት እና ማጽደቅ ኮሚሸኑ ወደ ስራ መግባቱ ገልጽው በአውደ ጥናቱ ለተገኙት የተለያዮ ቀጠና መሪዎችም የኮሚሽኑን የ10 ዓመት ስልታዊ አቅጣጫ እና የ5 ዓመቱን ዕቅድ በተመለከተ ሰፍ ያለ መብራሪያ አደርገዋል፡፡



የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ወይታ ወዛ በበኩላቸውም ቃለ-ሕይወት ቤተክርስቲያን አሁን በዚህን ጊዜ ነቅታ ወደ ቅንጅታዊ አሰራር መምጣት አለባት፣ ሁኔታውም ያስገድዳል፣ አሰራሩም ይፈቅዳል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል መርሆች መመሪያ ይሰጣሉ ይመሩናልና ለነዛ ደግሞ መታዘዝ አለብን የሚል አቋም መያዙን ገልጸዋል።
አክለውም ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ወይታ ወዛ አሁን በየቤተክርስቲያኑ ከአጥቢያ ጀምሮ ብዙ ልማታዊ ስራዎች ይሰራሉ። ከውጪ በሚገኘውም ደግሞ እርዳታ ፕሮጀክትን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ቃለ-ህይወት ቤተክርስቲያን ሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ስራውን ይሰራል። እነዚህ ሁለቱ ልማታዊ አውታሮች በአንድነት በመቀናጀት በጣም ተጠናክረው ቢቀጥሉ በሀገሪቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ትልቅ ሰራዊት ያለው ቤተክርስቲያን ቃለ-ሕይወት እንደሆነ ልንገነዘብ ችለናል።
ከተለያዩ አራት ቀጠናዎች የመጡ የቤተክርስቲያን መሪዎችና ተሳታፊዎች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ፥ በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፥ አገልግሎቱን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መምራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት መደረጉን በኮሚሽኑ የአስቾኳይ ግዜ እርዳታ እና መልሶ መቋቋም ፕሮግራም ማናጀር አቶ አብርሃም አላምቦ ተናግረዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ ለመንፈሳዊውም ሆነ ለልማት እንዲሁም ለሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች በቂ መሰረትና ትምህርት ያለው በመሆኑ፥ መሪዎችና አገልግሎቱ በዚያው ልክ ሙሉ መልእክቱን እንዲተረጉሙና ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል። የማኅበረሰብ ልማት ስራዎችን በምናከናውንበት ወቅት ሁልጊዜ ወደ ውጭ አገር እርዳታ ብቻ ከመመልከት ይልቅ፤ በአካባቢው ያለውን ሀብት በጥራት ጥቅም ላይ ማዋልና ያለውን ክፍተት መልሶ ማየት እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት የተገኘበት መሆኑ አቶ አብርሃም ተናግረዋል።
በተጨማሪም፣ የተጀመረው የተቀናጀ እቅድ ውጤታማ እንዲሆን በአውደ ጥናቱ ከተሳተፉ 4ቱ ቀጠናዎች ባለፈ እስከ ህብረቶች እና እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ መውረድ እንዳለበት አቅጣጫ ተመላክቷል። አጥቢያዎች ይህንን መመሪያ በዓመታዊ እና በስልታዊ እቅዳቸው ውስጥ በማካተት፣ በአካባቢያቸው ያሉ የትምህርት፣ የደከሙ ሰዎችን የመርዳት፣ የቤት ግንባታ እና የተፈጥሮ አደጋ ምላሾችን ከስብከተ ወንጌል ጋር አቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ጥሪ የቀረበ ስሆን በአውደ-ጥናቱ የተገኙቱ የቀጠና እና የቤተክርስቲያ መሪዎችን በዚህ ጉዳይ ላይ ሀላፍነታቸውን ለመወጣት ቃል በመግበት አውደ-ጥናቱ በስኬት ተጠናቅቋል።

Add a Comment