7G0A0263

ኮሚሽኑ ከሰራተኞች ጋር በመወያየት የፀደቀውን ስልታዊ ዕቅድ መተግበር ጀመር

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ቦርዱ ሰብሳቢና የቦርዱ አማካሪ ኮሚቴ ተወካዮች ቦርዱን በመወካል የአድሱን የኮሚሽኑን የስልታዊ ዕቅድ አተገባበር ማሳወቅን አላማ ያደረገ ስብሳባ ከኮሚሽኑ ሰራተኞች ጋር ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም    በጉዲና ቱምሳ ስብሳባ ማዕከል አደረጉ::

ስብሳባውን በጽሎት እና በአምልኮ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ወይታ ወዛ ያስጀመሩ ስሆን የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ ቦርድ ሰብሳብ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ የእግዚአብሔርን ቃል ከዘፀዓት 18፡17-27 ያለውን ክፍል አካፍለዋል፡፡ ከሙሴ ሕይወት የሚንማረው መሪ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ተማኝ እና ያልተገባ ጥቅም የማይፈልግ ወይም ሙስና እና ጉቦ አጥብቆ የሚጠየፍ መሆን እንደአለበት ነው ብለዋል፡፡

እንደ መሪ እና አገልጋይ ሰራተኛ ግልጽ የሆነ አሰራር እና ስልት መከተል በስራ ውጤታማ እንዴምያደርግ ተናግረው አንድ ሰው ሁሉንም ነገር መድረግ ወይም መሆን አይችልም ያሉት ሰብሳብው ግልጽ የሆነ አሰራር በመዘርጋት፣ስልት በመከተል እና የስራ ድርሻ በመስጠት መምራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ስልታዊ ዕቅዱን በተመለከተም ለሰራተኞች ገለጻ ያደረጉ ስሆን በዋናነትም ራዕይ፣ተልዕኮ፣ እሴቶችን ጨምሮ ተቋማዊና አስተዳደርዊ ተሃድሶ፣ተጠያቅነት እና በለአደራነትን በተመለከት ምን መምሰል እንደአለበት በስልታዊ ዕቅድ ላይ የተቀመጠውን አቅጣጫ ለሰራተኞች አብራርተዋል፡፡ እንዲሁም የሕዝብ ግንኙነት እና ተግባቦት፣ የብዝነስ ፓርትነርሽፕ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ለሁለንተናዊ ለውጥ የአሰራር እና የሰው ኃይል ተሃድሶ አስፈላጊ መሆኑ ጠቅሰው እያደገ ያለ ተቋም ሁልጊዜ ተሃድሶ ያስፈልገዋል ምክንያቱም በዓለማችን ያለው የአየር ንብርት ለውጥ፣ጦርነትና ያልተረጋጋ የኢኮኖሚ ስርዓት ከለጋሽ ድርጂቶች የሚገኙ ድጋፎችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው፡፡ ልማት ኮሚሽኑ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በመሆን የአገር ውስጥ ሀብት በተቀናጀ መልኩ የመሰባሰብ እና የማልማት ስራ መስራት ያሰፈልጋል፡፡ ለዚህም ይህ ስልታዊ ዕቅድ እንደ ፉኖታ ካርታ ሆኖ ያገለግላል ያሉት የኮሚሽኑ ቦርድ ሰብሳብ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ ስለ ተቋማዊ ተሃድሶ ስናስብ ስለ ሰው ልማት እና አስራር እንጂ መዋቅር የመቀየር ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡ የለማ የሰው ኃይል ተቋምን ማልማት እና ድርጅታዊ ራዕይን ለማሳካት ይርዳል፡፡ ስለዚህ የሰው ኃይል ልማት እና የኮሚሽኑን አሰራር መዘመን አስፈላጊ እና ዋና የትኩርት አቅጣጫ ነው፡፡

የጸደቀውን የ10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ በተመለከተ ከሰራተኞች ጋር በመወያየት ስልታዊ ዕቅዱን መተግበር መጀመሩ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ተሎሬ ገልጽዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ም/ክ ፕሬዝዳንትና የኮሚሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ፣ የቦርዱ አድቫይዘሪ አባላት እንዲሁም ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ወይታ ወዛ እና ሌሎች የኮሚሽኑ አመራር እና ሰራተኞች በተገኙበት ስብሰባ ላይ ስልታዊ ዕቅዱን መተግበር መጀመሩን ኮሚሽነሩ የገለጹት ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ የኮሚሽኑን የ10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ዝርዝር ነገሮችን ለሰራተኞች ያቀረቡ ስሆን ስልታዊ ዕቅዱ በ4 ዋና ዋና ምሶሶዎች ማለትም ተቋሟዊ ልቀት እና ዘላቂነት፣የተቀናጀ እና ሁለንተናዊ ማህበርስብ ልማት፣ሰብዓዊ ድጋፍ እና የአስቾኳይ ጊዜ ምላሽ እና ስልታዊ ዕድገት፣ቀጣይነት እና ፕሮግራም ዴሊቨሪ ኤክሴለስ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የቀጣይ 10 ዓመት የታቀደው ባጄት ከ27 ቢሊዮን ብር እንደሚበልጥ በስልታዊ ዕቅዱ ላይ የተገለጸ ስሆን እ.ኤ.አ ከ2026-230 ድርስ የአምስት ዓመት በጄት ብቻም 12.4 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡ በዚህም 3.2 ሚሊዮን የሚደረሱ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጾል፡፡

ይህ ስልታዊ ዕቅድ አተገባበረም በ3 ምዕራፍ የተከፈለ ስሆን አንድኛው እ.ኤ.አ ከ2026-2028 ጠንካራ መሰረት ሚጣልበት፣ፓሌት የሆኑ ድጂታል መሳሪያዎችን እና የሚያሰሩ ሞዴሎችን የሚንለይበት ስሆን ሁለተኛው ምዕራፍ እ.ኤ.አ ከ2029-2032 ያለው ደግሞ ተደራሽነታችንን የሚናሰፋበት፣ አጋሪነታችንን የሚናጠናክርበት፣ የፈንድ/የገቢ ምንጫችንን የምናበዛበት ሰሆን ሶስተኛው ምዕራፍ እ.ኤ.አ ከ2033-2035 ተቋማዊ ዘላቂነት እና በብሔራዊ ፖሊሲዎች ላይ ተጽዕኖ የሚናደረግበት ነው፡፡

እንዲሁም በስብሳባው የተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች አንዱ የሆነው አቶ ተሸመ ደርሳ የተዘጋጀው ስልታዊ ዕቅድ እንደ ልማት ኮሚሽን ከየት ተነስተን ወደየት መሄድ እንዳለብን የሚያሳየን ፉኖታ ከርታ ነው፡፡ እንደ ሰራተኛ ለዕቅዱ መሳካት የሚጠበቅብኝን ለማድርግ እተጋለሁ ስል ሀሳቡን አጋርቷል፡፡

በስልታዊ ዕቅዱ መንፈሳዊ እና የልማት አገልግሎት በመቀናጀት በእግዚአብሔር መንግስት ስራ ላይ ያለው ሚና በጉልህ በመቀመጡ በጣም አስደስቶኛል ያለችው ደግሞ የኮሚሽኑ ሰራተኛ የሆነችው ተስፋሽ በአምላክ ሞላ ናት፡፡

ስልታዊ ዕቅዱ ከቤተክርስቲያን ጋር በመቀናጀት ልማቱ ለወንጌል በር እንድሆን አብርን እንድንሰራ የሚያስተሳስር ዕቅድ ስለሆነ በዚህ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት የኮሚሽኑ ሰራተኛ የሆኑት አቶ እንዳለ ወ/ሳማያት ናቸው፡፡ አቶ እንዳለ ወ/ሳማያት አክለውም በስልታዊ ዕቅዱ የተካተቱ ነገሮች በሙሉ የበለጠ እንድንሰራ፣እንድንዘረጋ እና ልማት እና ቤተክርስቲያን በቅንጅት እንድሰሩ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *