የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የቦርድ አመራር በተዘጋጀው የኮሚሽኑን የ10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ላይ በጥልቀት በመወያየት ሚያዝያ 9 እና 10 2018 ዓ.ም የኮሚሽኑ ቦርድ የኮሚሽኑን የ10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ መጽደቁ የሚታወስ ነው፡፡
በስብሳባው መክፍቻ ላይ ለቦርዱ አባላት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ቦርድ ሰብሳብ እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ ይህኛው የቦርድ ስብሳባ በጣም ታሪካዊ እና የተለየ ነው ምክንያቱም ይህ የኮሚሽኑ 10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ተወያይተን የምናጽድቅበት እና የቤተክርስቲያኒቱን የ100 ዓመት ክብር በዓል ለማክበር ዋዜማ ላይ ነን፡፡ በዚህ ሁኔታ አድሱን ምዕተ ዓመት በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀውን ይህን የኮሚሽኑን ስልታዊ ዕቅድ ማጹደቁ ታሪካዊ ያደረገዋል ብለዋል፡፡





አንድ ነገር ሁልጊዜ መርሳት የሌለብን የቤተክርስቲያናችን አገልግሎት ስናስብ ልማትን አሁን በለችበት ቀርጽ ብቻ ማሰብ ተገብ ነው ብየ አላምንም፡፡ ብዙ ጊዜ ልማት ስናስብ አንድ ሰዎችን የሚረዳ ገንዘብ ያለው ሀብታም ልማት የሚሰራ ድርጅት ነው ብየ አላሰብም፡፡ ምክንያቱም ይህ ስራ የቤተክርስቲያናችን ተልዕኮም ጭምር ነው፡፡
የልማት ስራ የወንጌል አገልግሎት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በተዛባ አመለካከት ልማቱ መንፈሳዊ ስራ የማይመስላቸው አሉ፡፡ አንደአንድ አገልጋዮችም ጭምር ልማቱን ተውት ይላሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ ምክንያቱ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የጥሪዋ አካል ነው ልማት፡፡ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማትን አሁን በምንሰራው በፕሮፖዛል እና በፕሮጀክት ማኔጅመንት አይደለም የጀመረችው፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ልማት የጀመረችው በ1960ዎቹ አይደለም፡፡ ገና ከቤተክርስቲያኒቱ ተከላ ጀምራ ልማትን ስትሰራ የቆየች ቤተክርስቲያን ነች ፡፡
ምን አልባትም በሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ስራ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመንግስት ጎን የቆመች ትልቅ ቤተክርስቲያን ነች…፡እኛ ዛሬ የምናገለግለው አገልግሎት በብዙ መሰዋትነት የመጣ መሆኑን ሁሌ ልናስብ ይገባል፡፡ ስለዚህ ይህ ስራ እና አገልግሎት እንደት እንደመጣ ስናስብ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ራዕይ የልማት ኮሚሽኑ ራዕይ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ራዕይ አይነጣጠልም፡፡
ቴክንካል የሆኑ ነገሮች ልኖሩ ይችላሉ ነገረ ግን አንድ ራዕይ ነው ምኖረው፡፡ ስለ ቃለ ሕይወት አጥቢያዎች ይህ አካል ያስባል ማለት ነው፡፡ ስለ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ያስባል ማለት ነው፡፡ ስለ ደቀ መዝሙርነት ያስባል ማለት ነው በሌላ በኩል፡፡
ስለ ቤተክርስቲያን ተሃድሶ ይህ ልማቱ ያገበዋል ማለት ነው፡፡ ኮሚሽኑ ልማታዊ ነገር ብቻ የሚከውን ተቋም አይደለም፡፡ ዋና ስራው ወንጌል ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ከወንጌል የተወለደ ወንጌልን የሚያደርስ ስለሆነ፡፡ ሉቃ 10፡25-37 ያለውን የደጉን ሳምራው ታርክ ታውቃላቹሁ፡፡ አሁን የሉም እንጂ ያኔ ልማት ይሰሩ የነበሩ አባቶችን ብንጠይቅ እሱን አይተው የጀመሩ ይመስለኛል፡፡ ያለ ዘር፣ ያለ ሀይማኖት ልዮነት፣ያለ ቋንቋ ለሁሉም ሰዎች ድጋፍ እንድታደረግ የቤተክርስቲያን ጥሪ ነው፡፡ አሁን እኮ እንደዚህ ነው፡፡ አካታችነት እንላለን፡፡ ቃላቶች ተሽሞንምኖ መጡ እንጅ ቃለ ሕይወት ቀደማ አስባለች፡፡
ቃለ ሕይወት ቀድማ በውስጥዋ ድሆች እንኳን እያሉ ድሆችን መገልገል ተልዕኮ አድርጋ የኖረች ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ምክንያቱም ወንጌል ለድሆች ይሰበክ ዘንድ የተነገር የእግዚአብሔር ሀሳብ ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ይህን ሁሌ ማሰብ አለብን፡፡ እኔ ሁሌ ልማትን ሳስብ በዚህ ልክ ከልሆነ ልንሳሰት ወይም በተፈለገው ልክ ምላሽ ላንሰጥ እንችላለን፡፡ በልማት ስራ ውስጥ የሚንከውናቸው ነገሮች የተልዕኮችን አካል ነው፡፡ የሰውን ሁለንተና የማገልገል አካል እንጅ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ልማት ቀድሞ ይሄድ እና በልማት ስም ወንጌል እንስብክ የሚባለው አካሄድ ልክ አይደለም፡፡
ልማት ወንጌልን ለመስብክ እንደ መንደርደሪያ መደለያ አይደለም ወንጌል እራሱ ነው፡፡ ሰው ኮንቨክሽን ላይ ሚመጠው በራሱ ውሳኔ ነው፡፡ እኛ ግን ላልሰሙ ሰዎች ድጋፍ ስናደርግ ከእግዚአብሔር የተቀበለነው አደራ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ቦርድም ስለ ልማት የምናስበው እና የምንሰጠው ቦታ ምን አይነት ነው ሚለው ማሰብ ይፈልጋል?
በጣም ጌታን እንድናመሰግን ከሚገባን ምክንያት 100ኛ ዓመት ለማክበር ስንዘጋጅ እግዚአብሔር እንደ ቤተክርስቲያናችን ተሃድሶ የሚያመጣበት ጊዜ ነው፡፡ ልማታችን በሚቀጥለው ምዕተ ዓመት ለሚመጡ ትውልድ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ጋር በደንብ በተቀናጀ መንገድ faith development integration የሚንለው ሀሳብ ተጠናክሮ የሚሄድበት ነው፡፡ የቦርዱም የስብሳባው ዋና አጀንዳ አንዱ ይሄ ነው፡፡ እኔ ባደኩበት ቤተክርስቲያን የልማት ስራ ተብሎ አንድ አንድ ቀን ተመድቦ ልማት ይሰሩ ነበረ፡፡ለአቅመ ደካሞች ቤት ይሰሩ ነበረ፡፡ ይህ ልማት ነው፡፡ በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን 12 ሺህ አጥቢያ እንደየአቅሙ የሚሰሩት የልማት ስራ በገንዘብ ቢተመን ከለጋሽ ድርጅቶች ከገኜነው ይበልጣል፡፡ በደምብ ያንን የሚንመዘግብበት ሥርዓት የለም፡፡ ቤተክርስቲያን ለመንግስትም ለአገርም ይህን ታደረጋለች ብለን የሚናሳይበት ሥርዓት የለም እንጅ ይህ ትልቅ ነገረ ነው፡፡ በማዕከላዊነት ስራዎችን የሚሰንድ ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡
ቃለ ሕይወት አቅም እና ብቃት ስለላት ነው ብዙ ለጋሽ ድርጅቶች አብሮ ለመስራት የወሰኑት፡፡ እግዚአብሔር ራዕይ ስለሰጣት ነዉ፡፡ እንዳትረሱ ይህንን እግዚአብሔር ላልተማሩ አባቶች ጥበብን እና ትልቅ ራዕይን ስጥቶ ነበር፡፡ ቃለ ሕይወትን የወንጌል፣የአገልግሎት እና ልማት ስራዎችን በማዕከላዊነት ማስተባብር እንድቻል ብሔራዊ ዋና ጽ/ቤት እስከ ማቋቋም የሰሩ፤ከዚህም በኋላ ወንጌል ሙሉ የሚሆነው ልማት ስኖር ነው፡፡ ክርስቶስ ወንጌልም ይሰብካል፡፡ ምግብ ለሌላቸው ምግብ ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ይህንንም እንስራ ያሉ አባቶች ናቸው እንጂ አሁን እዚህ ያለን ሰዎች የደረስንበት አይደለም፡፡ ራዕይ ነው፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ ቃለ ሕይወትን ብንመለከት የቃለ ሕይወት የቀደሙ አባቶች ግልጽ ራዕይ-መነሻ እና መዳረሻ የነበራቸው አባቶች እና እናቶች ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር ራዕይ ያላቸውን አባቶች እና እናቶችን ስለሰጠን ቤተክርስቲያናችንን ዛሬ እኛ በደረስንበት ቦታ እንድትደርስ መረተዋታል፡፡ ለዚህም እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ፡፡
ለብዙ ቤተ-እምነቶች የቃለ ሕይወት የወንጌል እና የልማት አካሄድ እንደ መነሻ እና ሞዴል ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በአንድ ተቋሚ በአንድ አመራር ውስጥ በአንድ እይታ ይመሩት ነበረ አባቶቻችን፡፡ በዚህም ስኬታማ ነበሩ፡፡ ስለዚህ በሚቀጥለው ዘመን፡በእኛ ጊዜ ይህን አደራ እንደተረከበ ትውልድ በስራዎቻችን ምን ያህል ወንጌል እየተስፋፋ ነው፡፡ ምን ያህል ከወንጌል ስራ ጋር አብሮ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ በዚህ አቅጣጫ ነው ልማቱ መቃኘት ያለበት፡፡ ኢየሱስ የሰውን ሁለንተና እንዳገለገለ ቃለ ሕይወትም ሁለንተናዊ አገልግሎት ነው የሚታገለግለው በልማቱም ሆነ በመንፈሳዊ አገልግሎቷ፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ ለማደግ ብዙ ጥረት እያደረገች እንደሆነ ታውቃላቹሁ፡፡ የ10 ዓመት ዕቀድ ታቅዶ አገሪቷን ለማበልፀግ፡ ሰዎች ከድህነት እንደወጡ እና የተሸለች አገር እንድትሆን ብዙ ነገር እየተሰራ ነው ከእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቀድ ጀምሮ አሁን ደግሞ ሀገር በቀል እኮኖሚ ልማት ፕሮግራም በመንግስት በኩል፡፡ የኢትዮጰያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ከመንግስት የዕድገት እና ልማት ጋር የተገናኘ ስራ ነው የሚትሰራው፡፡ ብዙ አስተዋጾኦ ያደረጋል፡፡ መንግስት ይህን ዕቅድ ሲያዘጋጅ ብቻውን አይደለም የሚሰራው፡፡ የሀይማኖት ተቋማት እንዲሰሩ ይፈልጋል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሰሩ ይጠብቃል፡፡ በተለይም ቤተክርስቲያን ከተከታዮቻቸው ፣ከሞራል ግንባታ ፣ከስነ-ምግባር አንጻር ብዙ ሚና እንደሚትጨውት ይታመናል፡፡ የእኛን ቤተክርስቲያን አስቡ 12 ሚሊዮን ሕዝብ በስነ-ምግባር እና በሞራል የታነጸ ብሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደ መልካም አቅጣጫ መቀየር ይችላል፡፡ በዚህ ልክ መስራት ነው ከእኛ የምጠበቀው፡፡ ለዚህ አስተዋጾ የሚያደረግ ስልታዊ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ፀድቋል፡፡ ሁላችንም የሚመለከተን በለድርሻ አካላት ለተፈጻሚነቱ እንትጋ፡፡
አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ ቦርድ ሰብሳብ

Add a Comment