ኮሚሽኑ ከከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የምስጋና ምስክር ወረቀት እና ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የምስጋና ምስክር ወረቀት እና ዋንጫ በዛሬ ዕለት ተሸላሚ ሆኖል፡፡

ኮሚሽኑ በአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቆሼ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረደ 13 እና ኮልፌ ቃራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ወይም በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በምጠራው አከባቢ  የኮሚሽኑ  የምገባ ፕሮጀክት ለደረገው አስተዋጾ ከከተማው አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ምስገና እና ዕውቅና ተችሮታል፡፡

ኮሚሽኑ በዚህ አከባቢ ለሚገኝ በ162 አቅመ ደካሞች ምግብ እና ምግብ ነክ ድጋፎች ለለፉት 8 ወራት የሰጠ ስሆን ለዚህም በጎ ተግባር ምገባ ኤጄንስው ኮሚሽኑ ለሳካው ከፍተኛ የስራ አፈጻጽም በዛሬው ዕለት የሰርቲፍኬት እና የዋንጫ ሽልማት ዕቀወቅና መሰጠቱን ለስራችን አበረታች ነው ስሉ በኮሚሽኑ የቆሼ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አክልሉ ገ/ሕይወት ተናግረዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት በሳማሪታን ፐርስ(Samaritan purse) በተገኜ 19 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የሚተገበር በምገባ፣ዋሽ፣በራስ አገዝ ቡድን ልማት እና በሁለንተናዊ መልኩ መለወጥ እንድችሉ የሕይወት ክህሎት(አቅም ግንበታ ስልጠና) ላይ ትኩረት አድረጎ የምሰራ ፕሮጀክት ነው፡፡

የዕለት ጉርስ ለማግኘት ለሚቸገሩ 162 እናቶች ማለትም 132 ሴቶች ፣18 ወንዶች እና ለ12 ሕጻናት የምገባ እና የተላያዮ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ አሁን ላይም ከምገባ በለፈ 100 ሰዎችን 5 የራስ አገዝ ቡድኖችን በማደራጀት የቁጠባ በህላቸው እንድያደብሩ እና በገቢ እራሳቸውን እንድደግፉ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የ5ቱም የራስ አገዝ ቡድን ቁጠባቸው አሁን ላይ እያደገ ስሆን ከራስ አገዝ ቡድን በተመቻቸላቸው የውስጥ ብድር አገልግሎትም 42 የሚደረሱ እናቶች አነስተኛ የንግድ ስራ ጀምረው ኑሮቸውን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ ዛሬ የተበረከተልን የዕውቅና የሰርቲፍኬት እና የዋንጫ ሽልማት ለእኛ የተበረከተ ብሆን ይህ እውን እንድሆን በተለያየ መንገድ ድጋፍ ስያደረጉ እና ስያስተባብሩ የነበሩትም የዚህ ሽልማት በለቤት ናቸው ብለው  ሠፈረ ሠላም ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያንን፣የፕሮጀክት ሰራተኞችን፣ኮሚሽኑን ፣ሳማሪታን  ፐርስ(Samaritan purse) እና የመንግስት በለድረሻ አካላትን ለደረጉት መልካም አስተዋጾ አቶ አክልሉ አመስግነዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *