




ሴቶች በማህበራዊ፣እኮኖሚያዊ እና ፖሎቲካዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት እና በእኩልነት ማሳተፍ ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን ሥርዓተ ጾታን መርዳት እና ጾታዊ ጥቃትን መከላከል ሴቶች ያላቸውን እምቅ አቅም መጠቀም እንድችሉ ከማስቻል በሻገር ለአገር ግንባታ፣ለማህበራዊ እርቅ እና ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ያላቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አቶ እንዳለ ወ/ሰማያት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ጂስራ ፕሮጀክት ኃላፊ ተናግረዋል፡፡

በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ዶሬ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲን በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ለታደሙ ተሳታፊዎች ስልጠና የሰጠው የትግባራ ስነ-መለኮት ምሁር እና የጋብቻ አማካሪ ዶ/ር ይደነቃቸው መለሰ ነገሮችን ሁሉ በመከባበር እና በፍቅር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሴቶች እኩልነት እና ለእርቅ ያለቸው ሚና ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው እኩልነት፣አስፈላጊነት፣ጠቃሚነት እና ውሳኔ ሰጪነት በተመለከተ የሴቶችን ሚና መልካም እና አስፈላጊ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ በመሆኑም የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ለሁለንተናዊ ዕድገት እና ሠላማዊ ማህበረሰብ እና አገር ለመገንባት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ አስቴር፣ኑሀሚን፣ሩት ሴት እህቶች ሲሆኑ ነገረ ግን በጊዜው ለተፈጠሩት የተለያዮ ችግሮች መፍቴሔ እና መውጫ መንገድ እንድፈጠር ጠንካራ ውሳኔ በመወሰን እራሳቸውን እና ማህበረሰባቸውን ከጥፋት መዳን ችለዋል፡፡ ዛሬም የሴቶች እኩልነት እና አስታራቅነት ሚናን ማህበረሰባችን በዚህ አውድ መረዳት እና መተግበር ያስፈልጋል ስሉ ዶ/ር ይደነቃቸው ገልጸዋል፡፡
ሳልጣኞችም ስልጠናው መልካም እና በአከባቢያቸው የሚስተዋሉ ጎጂ ልማዳዊ ልምምዶችን ለማስቀረት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው ስለ ሥርዓተ ጾታ፣ ጾታዊ ጥቃትን መከላከል እና የሴቶች ድርሻ በማህበረሰባዊ እርቅ ስርዓት ላይ በንቃት እንድሳተፉ ለማድረግ መሰል የግንዛቤ መስጨበጫ መድረኮች እና ዘመቻዎችን ለሰፊው ማህበረሰብ መሰጠት እንደሚገባ ጦቁመዋል፡፡








እንዲሁም ኮሚሽኑ በሻሽመኔ ለሚገኙ የራስ አገዝ ቡድን ተወካዮች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ወንጌላዊያን እና ለቁልፍ በለድርሻ አካላት ለዘላቂ ሠላም ግንባታ እና ሀብት ማሰባሰብ ላይ ትኩርት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና አካሂዶል፡፡ ስልጠናውም ታሳታፊዎች በእጃቸው እና በአከባቢያቸው ያላቸውን ሀብት ላይተው እንድያውቁ እና እንድሰሩ በማድረግ እና ለዘላቂ ሠላም ግንባታ የበኩላቸውን ሚና ማድረግ እንድችሉ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡



የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሀይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት በሀላባ፣ስልጠየ፣ ወራቤ፣ሻሽመኔ፣ነጌሌ አርስ፣ምዕራብ አርስ እና ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ለለፉት 5 ዓመታት በርካታ የሠላም ግንባታ፣ግጭት አፈታት እና መሰል በርካታ ጉዳዮች በእነዚህ አከባቢዎች እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን በወሃ፣በጤና፣በግብረና፣በትምህርት፣በራስ አገዝ ቡድኖች በማደራጀት፣ በአስቾኳይ ጊዜ እርዳታ እና መልሶ ማቋቋም በአገር አቀፍ ደረጃ ከግማሽ ክፈለ ዘመን በላይ ያለማቋረጥ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ሀይማኖታዊ የልማት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋም ነው፡፡
Add a Comment