
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሀይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት በሀላባ ለሚገኙ የራስ አገዝ ቡድኞች፣ የቤተክርስቲን መሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሀላባ ከተማ ያለፈው አርብ ቀን አካሂዶል፡፡



የአንድ የራስ አገዝ ቡድን ቁጠባም ከሩብ ሚሊዮን ብር በላይ በድረሱን ተጦቁሟል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሀይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት የሥራ ጊዜውን ስጨርስ በአከባቢው የተመሰረቱ የራስ አገዝ ቡድኖች የቁጠባ እና የሥራ እንቅስቃሴ ቀጣይነት እንድኖር ተስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
ስልጠናውም በጸሎት እና የእግዚአብሔርን ቃል በመካፈል የተጀመረ ስሆን አቶ ደስታ ሔላሎ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኮሚሽኑ የጄስራ ፕሮጀክት አስተባበሪ ስለ ራስ አገዝ ቡድን ፅንሰ ሀሳብ፣አመሰራረት፣የራስ አገዝ ቡድን መደራጀት እና መቆጠብ የሚያስገኘውን ጥቅም እና መልካም ጉኞች በተመለከተ ለመጡ ለስልጣነው ተሳታፍዎች ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም አቶ እንዳለ ወ/ሳማያት በኮሚሽኑ የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሀይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት ማናጀር/ኃላፊ ስለ ሥራ ፈጠራ/እንተርፕረነርሽፕ ሰፋ ያለ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡



ሳልጣኞችም ስልጠናው መልካም እና የራስ አገዝ ቡድን የሥራ እንቅስቃሴን ለማስቀጠል አቅም የሚሆናቸው መሆን ገልጸዋል፡፡ በሀላባ የሚገኙ የራስ አገዝ ቡድኖች ቁጥር ስመሰረት 10 አከባቢ ስሆን በአሁኑ ላይ 8 የሚሆኑ የራስ አገዝ ቡድኖች በጥሩ ሁኔታ ሳምንታዊ ቁጠባቸውን እያካሄዱ የሚገኙ ስሆን ለአብነትም የአይነቆሬ የራስ አገዝ ቡድን ቁጠባቸው ከ350ሺህ ብር በላይ መድረሱን ተጠቁሟል፡፡



ፕሮጀክቱ በአከባቢው የሠላም ግንባታ ሥራዎችን ከመስራቱ በሻገር ማህበረሰቡን በማሰልጠን እና በራስ አገዝ ቡድን በማደራጀት ኑሮአቸውን እንድደግፉ እና ኢኮኖሚያቸውን እንድያሳድጉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ በሻገር በቤተ-እምነቶች መቀራረብ እና መነጋጋር እንድዳብር በማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር መልከ-ብዙ ግጭቶች እንድቀንሱ እና እንዳይከሰቱ በማድርግ አመረቂ ውጤት መገኜቱን ተሳተፊዎች ገልጸዋል፡፡


የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሀይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት በሀላባ፣ስልጠየ፣ ወራቤ፣ሻሽመኔ፣ነጌሌ አርስ፣ምዕራብ አርስ እና ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ለለፉት 5 ዓመታት በርካታ የሠላም ግንባታ፣ግጭት አፈታት እና መሰል በርካታ ጉዳዮች በነዚህ አከባቢዎች እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን በወሃ፣በጤና፣በግብረና፣በትምህርት፣በራስ አገዝ ቡድኖች በማደራጀት፣ በአስቾኳይ ጊዜ እርዳታ እና መልሶ ማቋቋም በአገር አቀፍ ደረጃ ከግማሽ ክፈለ ዘመን በላይ ያለማቋረጥ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ሀይማኖታዊ የልማት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋም ነው፡፡
Add a Comment