አድስ አበባ፡-የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን አዲስ ለተሾሙት የቦርድ አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ እና በቦርድ አመራር እና አባል ሆነው ሲያገለግሉ ለቆዩትን የምስጋና የእውቅና መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጽፈት ቤት ሰኔ 27/ 2017 ዓ.ም አካሄዷል።
















በመርሃ ግብሩ ለነበሩ የቦርድ አመራር የሽኝት የተደረገ ስሆን ለአድሱ ቦርድ የኮሚሽኑ የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦል፡፡ የቀጣይ አምስት ዓመት ስልታዊ እቅድ አሰራር በሚመለከት ጋር ሰፊ ውይይት ከአድሱ ቦርድ ጋር ተደርጎል።
እ.ኤ.አ በ2025 በግማሽ በጀት ዓመት ስራ ላይ የዋለው የገንዘብ መጠን 703.6 ሚሊየን ብር ሲሆን ከበጀት ዓመት እቅድ ጋር ሲነጻጸር 96.2% አሳይቷል፡፡ ይህ የበጀት አፈጻጸም ከ2024 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር 250.8 ሚሊየን ብር(55.3 %) ብልጫ ማሳየቱን በሪፓረቱ ተጠቅሶል፡፡ በተሰሩ የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ስራዎችም 276 ሺህ ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ መድረስ መቻሉን በሪፓረቱ ተገልጾል የሆኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ 49 በመቶ ነው፡፡
የውስጥ አሰራር ሄድቶችን አጠናክሮ ከማስቀጠል አዃያ ኮሚሽኑ በትጋት መስራቱን በመርሃ ግብሩ መድረክ ላይ ያነሱት የቀድሞ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን የቦርድ ሰብሳቢ ወይም አሁን ላይ የቤ/ክቱ ፕሬዝደንት ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ በአንድነት እና በጋራ በመሆን ብዙ ስራዎችን መስራት እንደሚቻል የተናገሩ ሲሆን አዲስ የተመረጡ የቦርድ አመራሮች የስራ ቆይታቸው መልካም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጽዋል ።








የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ቦርድ ሰብሳብ ዶ/ር ስማኦን ሄሊሶ ጨምሮ በቦርድ አባልነት ልማት ኮሚሽኑን ለአገለገሉት አካላት የእውቅና ሰርቲፍኬት እና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት ጸሎት በማድረግ የተጀመረው የግማሽ ዓመት የቦርድ ስብሰባ ዶ/ር ተስፋዬ ያዕቆብ ዘጸአት 18 ፤ 19 ላይ ያለው የኢግዚአብሔርን ቃል በማካፈል ሥነ-ሥርዓቱ ተካሄዶል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ፕሬዝደት ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ ፤ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት ፤የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ም/ፕሬዝዳንት እና የኮሚሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ጫዕሜቦ ፤ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ፣ የቦርድ አባላት እና ፕሮግራም ዳይሬክተሮች እና የፕሮጀክት ስራ አስተባበሪዎች ተገኝተዋል።
አዲሱ ቦርድ ከልማት ኮሚሽኑ በቀረቡ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ወሳኔዎችን በመወሰን ስበሰባዉ ተጠናቋል፡፡

Add a Comment