ኮሚሽኑ ወሃን ቤት ውስጥ ማከም እና ከብክላት ጠብቆ ማቆየት ላይ ያተኮረ የልምድ ልዉዉጥ ስብሰባ አደረገ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ወሃን ቤት ውስጥ ማከም እና ከብክላት ጠብቆ ማቆየት ላይ ያተኮረ የልምድ ልዉዉጥ ጉባኤ/ስብሰባ  ከባለድርሻ  አካላት  ጋር   ከግንቦት 20-21/2017 ዓ.ም በአድስ አበባ ጁፕተር ሆቴል አደረገ፡፡

በሁነቱ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ዋይታ ወዛ ጨምሮ ከጤና ሚንስቴር፣ከወሃ እና ኢነርጂ ሚንስቴር እንዲሁም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከጤና ፣ወሃ እና ኢነርጂ እና ስራ ዕድል   ፈጠራ ቢሮዎች እና ከተለያዮ ግብር ሰናይ ድርጅት የተጋበዙ የመንግስት በለድርሻ አካላት በስብሳባው ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ዋይታ ወዛ በመክፈቻ ንግግራቸው ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ የልማት እና ሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች ብለው አሁን ላይም በልማት ኮሚሽኑ በኩል በመላ ሀገሪቱ በምባል ደረጃ በርካታ  ፕሮጀክቶችን በውሃ፣ በጤና፣ በማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻልና በአደጋ ምላሽ፣ በትምህርት፣ በማህበራዊ አገልግሎት እና አቅም ግንባታ እና ሌሎች  ማህበርሰብ ተኮረ የልማት ፕሮግራሞች በመቅርጺ እየሰራች መሆኑን ዶክተር ወይታ ገልጸዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ እንደ አገር የሚያገለግሉትን ሆስፒታሎችን ከአጋር አካላት ጋር በመክፈት ለአገሪቱ ጤና ዘርፍ ቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጓንም አክለው CWAST የ15 ዓመት አጋራችን ነው። በተለይም ባለፉት ሶስት አመታት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል   በተሰሩ ስራዎች ማህበርሰቡ ወሃን አክመው የመጠጣት በህል ማሳደጉን ገልጽዋል፡፡ ይህ ሥራ በካባታ ዞን-ቃጫ ብራ ወረዳ ፣ሀዲያ ዞን-ምሻ ወረዳ እና ጉራጌ ዞን-አበሽጌ ወረዳ  በስምንት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እየተሰራ ነው።

ዛሬ፣ ይህ ጉባኤ የመጠጥ ዉሃን ቤት ውስጥ አክሞ መጠቀም እና ከብክለት ጠብቆ ማቆየት ላይ  ጠቃሚ እውቀትን እና ልምድን እርስ በእርስ ለመለዋወጥ ምቹ መድርክ መፍጠሩን ገልጽው ይህን ፕሮጀክት በገንዘብና በአስፈላጊ ነገሮች ድጋፍ ላደረጉ ለጋክ(GAC) እና (ከዋስት)CWAST እና የመንግስት አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርቧል።

ጤና ሚኒስቴርን ወክለው በሁነቱ የተገኙት ተሳታፍም አብዛኛው የሀገራችን 60 በመቶ የጤና ችግሮች የምመነጩት የአካባቢ ጽዳት ጉድለት፣ ውሃን አክሞ በለመጠቀም እና የግል ንፅህና በለመጠበቅ ነው። ስለዝህ ህብረተሰቡ ያለውን ውሃ በማከም እንዲጠቀም የተቻለንን ሁሉ ማድረግ አሁንም ለነጌ የሚባል አይደለም። ከዚህ አንጻር ኮሚሽኑ እየሰራ ያለው ስራ ብዙዎችን ያሳረፈ እና ለጤናማ ሕይወት መሰረት የጣለ፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን ከወሃ ወለድ በሽታ የጠበቀ ነው፡፡

ይህ ፕሮጄክት በአበሸጌ፣ ሚሻ እና ቃጫቢራ ወረዳዎች በሚገኙ 16 ቀበሌዎች ላይ ትኩርት አድረጎ እየሰራ ስሆን 81,746 ግለሰቦችን በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነዉ፡፡

በተደረጉ የዋሽ ስልጠናዎች እና ድጋፎች የማህበረሰቡ ቤት ውስጥ ወሃን አክመው የመጠቀም ልምዳቸው ከ9 በመቶ ወደ 40 በመቶ ማደጉን በልማት ኮሚሽኑ የወሃ ጥራት ቁጥጥር ከፍተኛ በለሙያ አቶ አብይ ገዛኝ በቀረቡት ርፓርት አመላክተዋል፡፡

ከካናዳ የመጡት የከዋስት ፕሮጀክትም በለሙያዎች ወሃን ቤት ውስጥ አክሞ መጠቀምን እና ከብክለት ጠብቆ መቆየት እና የግል እና የአከባቢ ንጹሕና አጠበበቅ፣ አጋረነትን ማሳደግ፣የልማት ዘላቂነት ማረጋገጥ፣የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እና የውይይት በማድረግ ለቀጣይ ስራ የምሆን ግብዓት እና ልምድ ልውውጥ አድረገዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *