የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ተሎሬ እና በኮሚሽኑ የማህበራዊ አገልግሎት እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ወይታ ወዛ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ ዞን የተሰሩ የወሃ እና የትምህርት፣ የልጆች እና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክቶችን ጉብኝት አደረጉ፡፡













የመስክ ጉብኝታቸውንም ከመጋቢት 9/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም ያደረጉ ሲሆን በመስክ ምልከታቸው በምስራቅ ባሌ ዞን የተሰሩ የመጠጥ ውሀ እና የትምህርት ፣ልጆች እና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክቶችን ስራዎች ጉብኝት አድረገዋል። ከፕሮጀክቶች ጉበኝት ጎን ለጎንም በአከባቢው ከሚገኙ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን አጥቢያ እና ሕብረቶች ጋርም ጥሩ የጉብኝት፣የምክክር እና የጽሎት ግዜ አድረገዋል፡፡




የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ተሎሬ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት በዚህ አከባቢ 6 የመጠጥ ወሃ ጉድጓድ ለመቆፈረ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት ክፍት ለማድረግ በጀመረነው ስራ 12 ጉድጓድ ተቆፈሮ ነው 6 የሚሰራ የወሃ ጉድጓድ ለማህበረሰብ አገልግሎት ክፍት ያደረግነው፡፡
ይህን አይነት መስዋትነት ብዙ ድርጅቶች አይከፍሉም ምክንያቱም ቢበዛ ሁለት ወይም ሶስት ቦታ ቆፍረው ወሃው ከልተገኘ ትተው ይወጣሉ፡፡ እኛ(የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን) ግን በአከባቢ የከፋ የመጠጥ ወሃ ችግር እንዳለ ስለተረዳን፡ ከሚመለከታቸው በለድርሻ አካላት ሁሉ ጋር በቅንጅት በመስራት 6 የሚሰራ ጉድጓድ ለማህበረሰብ አገልግሎት ክፍት አድረገናል፡፡ በብዙ ሙከራ እና ተስፋ በለመቁረጥ ለዚህ ስኬት በቅተናል ስሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

አክለውም በዝህ ስኬት ላይ ብቻ መቆም ሳይሆን ይህን የተሰሩ የወሃ ጉድጎዶችን ወደ ሶላረ በመቀየረ እና በማስፋፋት ሰፍውን ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የአከባቢውን መንግስት በለስልጣናትን እና የወሃ ኮሚቴዎች በጉዳዮ ላይ በትኩረት እንድሰሩም ሀሳባቸውን ያንጽባረቁ ሲሆን ልማት ኮሚሽኑ እንደ አስፈላጊነቱ ቴክኒካል ድጋፍ በመስጠት ሊደግፍ ይችላል ብለው የተሰሩ ስራችንም በምልከታቸው አድንቀዋል፡፡





ይህ ከተማ ትልቅ ከተማ ነው፡፡ የከተማይቱን ዘረፈ ብዙ ችግር በጋራ በመስራት እንቀረፋለን የሚል እምነት አለኝ ሲሉ ሃሳባቸውን የገለጹት ደግሞ በኮሚሽኑ የማህበራዊ አገልግሎት እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ወይታ ውዜ ናቸው፡፡ የኮሚሽነሩን ሀሳብ የተጋሩት ዶክተር ወይታ ወዛ ለሁሉም ነገረ የእናንተ ተሳትፎ ውሳኝ ነው፡፡ እስካሁን ያደረጋቹሁትን አይተናል ነገረ ግን አሁንም ይህንን ወሃ ለሰፊው የከተማው ሕዝብ የማስፋፍያ ስራዎች ተሰረተው ማድረስ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ቁጭ ብላቹሁ ብትመክሩ የከተማው ማህበረሰብ የወሃ አቅረቦት ችግር መፍታት ይቻላል የሚል እምነት እንዳለቸው ተናግረዋል፡፡






በኮሚሽኑ የወሃ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ቸርነት ብርሃኑ በበኩላቸው በአከባቢው የሚስተዋለውን የመጠጥ ውሀ ችግር ለመቅረፍም ልማት ኮሚሽኑ 6 መለስተኛ የውሃ ጉድጓዶችን በምስራቅ በሌ ዞን በጊኒረ ወረዳ በ6 ቀበሌያት ማለትም ሀሊላ-1፣ ሀሊላ-2፣ዶቤ፣ ኤልቡኮ/ሀራዋ-8፣ኤልቡኮ/ሀዋ-2 እና ኤልቡኮ ሀራዋ ቀበሌያት በመቆፈር ለማህበረሰብ አገልግሎት ክፍት አድርጓል።ይህ የመጠጥ የወሃ ጉድጎድ ቁፋሮ እ.ኤ.አ. ኦክቶቨር(October 1/2023 እስከ ሴፕቴምበር/September 30/2024 የተሰራ ሲሆን አጠቃላይ ባጄቱ 6.5 ሚሊዮን ብር መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጾል፡፡
ይህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 10500 የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደረገ ስሆን ከዚህም ውስጥ 6000 ማህበረሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ የሆኑ ናቸው፡፡ ይህ የወሃ ፕሮጀክቱ ዋና አላማው በጎሎልቻና ጊኒር ወረዳ ለተመረጡ የገጠር ማህበረሰቦች ወይም መንደሮች በቂ የመጠጥ ውሃን በዘላቂነት በማቅረብ እና በንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረጉን አቶ ቸረነት ብርሃኑ ተናግረዋል።
የተቆፈሩ ውሃ ጉድጓዶችም ማህበረሰቡ ወሃ ፍለጋ በቀን 4 እስከ 10 ኪ.ሜ ይጎዙ የነበረውን በማሳጠር በአቅራቢያቸው ንፁህ የመጠጥ ወሃ እንድያገኙ ያድረገ ሲሆን ከንፅህና ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን ህመም እና ሞትን መቀነስ መቻሉንም አቶ ቸርነት ገልጽዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በጊኒር እና ጎሎልቻ ወረዳዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 38 በመቶ እና 42 በመቶ ሲሆን ይህም ወረዳዎቹ የመጠጥ ወሃ ሽፋን ላማሳደግ እንዲሁም የሀገሪቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ ትኩረትና ጥረት እንደሚያስፈልግ ማሳያ ስሆን ልማት ከሚሽኑ ወሃ ስራዎችም የወረዳዎቹን የወሃ ሽፋን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አተዋጾ እያበረከተ እንደሆነ በርፖርቱ ተገልጾአል፡፡

የኮሚሽኑ ቦርድ አባል አቶ ጉልላት ግዛዉ በበኩላቸው ልማት ኮሚሽኑ በዚህ አከባቢ የሚስተዋለውን ዘረፈ ብዙ ችግር በተላይ የወሃ ችግር ለመፍታት ያደረገውን ጥረት አድንቀው ልማት ኮሚሽን ዘር፣ቀለም፣ሀይማኖት ሳይላይ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ለሰው ልጆች ሁሉ እያደረገ ለለው ድጋፍ ልማት ኮሚሽኑን እና አመራሩን አመስግነዋል፡፡


የጊኒረ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው ማህበረሰባችን ወሃ ለመቅዳት በቀን ከ10 ኪ.ሜ ይሄዱ ነበረ፡፡ አሁን ያን ልፋት አስቀረታቹሃል፡፡ ልማት ኮሚሽኑ ሀይማኖታዊ ድርጅት ብቻ አይደለም ማህበረሰባዊ እና ሰውን ለመረዳት የቆመ እንደሆነ አውቀናል፡፡ እንደ መንግስት መድረስ እና መፈታት ያልቻልነውን የህዝባችንን ችግር ስለፈታቸሁ በህዛባችን ስም እናመሰግናለን፡፡
ይህንን የወሃ ችግራችንን እስከ ፌድራል መንግስት ድርስ አሳውቀን ነበር፡፡ መንግስት ችግራችንን ያውቅ ነበር ነገረ ግን መፍታት አልቻለም ነበር፡፡ ይህው ዛሬ በእናንተ በኩል የወሃ ችግራችን መፍትሔ በጥቅቱም ቢሆን አግኝቶል፡፡ ይህ ትልቅ ተስፋ ነው ለህዝባችን ሲሉ ገልጸዋል፡፡








ይህ የመጠጥ ወሃ በአቅራቢያችን በመቆፈሩ ዕድለኛ መሆናቸውን ገልጽው ይህን ወሃ በቅርበት መግኘታችን ልጆቻችን ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ አድረጎል፡፡ ወሃ ወለድ በሽታም ሆነ ሞት ቀንሶል፡፡ የሴቶች መደፈረንም ሆነ ጠለፋን ከመቀነስ አንጻር ከፍተኛ ሚና እየተጨወተ ይገኛል፡፡

Add a Comment