
አዳማ፡ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን በአዳማ ከተማ ለነጌ ተስፋ ራስ አገዝ ቡድኖች ማህበራት ጥምረት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
ትናንት መሰጠት የተጀመረው ስልጠናው ትኩረቱ ፕሮጀክት ማቅረጽ እና ማስተዳዳር፣ ማቀድ እና መተግበር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሲሆን የሰልጣኞችን ፕሮጀክት የመቅረጽ፤ የማስተዳደርን እና መተግበርን አቅም ከማሳደግ አንጻር የጎላ ሚና አለው፡፡








ስልጠናው ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ54 የሚበልጡ ተሳታፍ ሰልጣኞች ተግኝተዋል፡፡
የሰልጣኞችን አቅም ከመገንባት አንጻር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ ስልጠናውም ፕሮጀክት ከመቅርጽ እስከ መተግበረ ድርስ ያሉትን ጠቃሚ ሀሳቦች የሚነሱበት ይህ ስልጠናው ተሳታፍዎች በየአደረጃጀታቸው ክፍተታቸውን ለይተው በማውቅ ለፕሮጀክት ቀረጻ፣ማስተዳደር እና ትግበራ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዳ ስልጠና ነው፡፡

አቶ ድንቁ ሹሚ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብአዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻያ እና የአደጋ ጊዜ ሚላሻ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ በበኩሉ አሁን የሰራቹሁ ያላቹሁት የምትማሩበት ስራ ነው፡፡ ወደ ፊት የተሸለ ስራ ትሰራለቹሁ፡፡ አሁን እንደ ድርጅት ነው የሚትሰሩት፡፡ ድርጅት የራሱ አሰራር አለው፡፡ ለዛ ብቁ ለመሆን መስራት እና እውቀትን መሸመት ያስፈልጋል፡፡








እንደ አገር በቀል ድርጅት ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ ናቹሁ፡፡ ልማት ኮሚሽኑ እናንተን ለማብቃት ይሰራል፡፡ ልማት ኮሚሽኑ ከእናንተ ጋር ነው ግን ሁል ጊዜ ስራዎች እና ድጋፎች በልማት ኮሚሽኑ በኩል ላይቀጥል ይችላል፡፡ ለዛ ነው እናንተን መብቃት ላይ ልማት ኮሚሽኑ እየሰራ ያለው፡፡ ልማት ኮሚሽኑ ለለፉት ሁለት አስርት ዓመታት እናንተን ስያደራጂ፣ሲረዳ፣ሲደግፍ ቆይቶል፡፡ አሁን ግን እናንተ እንቅስቃሴ ወደ ድርጅትነት ስላደጋቹሁ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ እራሳቹሁን በራሳቹሁ የምታስተዳድሩበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ አሁን በሁለንተናዊ መልኩ እራሳቹሁን በማብቃት ድርጅታቸሁን ለማስተዳደር መዘጋጀት ያስፍልጋል ስሉ አቶ ድንቁ ሹሚ ገልጽዋል፡፡

አቶ ደምሴ ባቲ ልማት ኮሚሽኑ የእወቅት እና ማስተማረ ኤክስፕርት/Knowledge and Learning expert for Yenege Tesfa SHG Collectives ስልጠናውን በሚሰጥበት ወቅት ቀዳሚ ለሆኑ ለጥምረቱ አላማ፣ ግብ እና እሴቶችን ተገዢ በመሆን እና ለይቶ በማውቅ እና በመስራት ስኬታማነትን መቀዳጀት ይቻላል ብለዋል ::
የልማት ፕሮጀክት ዑደት አራት ደረጃዎች ስኖሩት፡- ፕሮጀክት ልየታ፣ ማቀድ፣ ትግበራ፣ ክትትል እና ግምገማ ሲሆን ይህን በትክክል የሚሰራ አካል ፕሮጀክት ውጤታማ ይሆናል፡፡ ችግሮች ሁሉ በአንዴ አይፈቱም ያሉት አቶ ደምሴ ባቲ ችግሮችን እንደ አንገብጋቢነታቸው ቅደሚያ በመስጠት መፈታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በዕቅድ ያልተመራ ሕይወት ለውድቀት የታቀደ ነው፡፡ ችግር ሁሌም አለ፡፡ ሁሉም ችግር በአንዴ አይፈታም፡፡ ስለዚህ ችግሮችን በሚገባ መለየት እና ለችግሮችም አንደ አንገብጋቢነታቸው በቅደም ተከተል ተለይተው በማቀድ መፍቲሄ ማብጀት ያስፈልጋል ብለው የስራ ድርሻን ለይቶ ማውቅ እና መስራት የፕሮጀክት ትግበራን ስኬታማነት ላይ የጎላ ሚና እንዳ አለውም አክለዋል፡፡
ሰልጣኞቹ ከስልጠናው በኃላ ሌሎች በስራቸው ለሚገኙ ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት እና ልምድ በማከፈል ማህበረስብ አቀፍ ለውጥ ለማምጣት እንድሚሰሩ ሀሳባቸውን ገልጽዋል፡፡ ፕሮጀክት መቅረጽ፣ማስተዳደር እና መተግበር ትልቅ ኃላፊነት ነው፡፡ ይህ ለእኛ እጅግ ጠቃሚ ስልጠና ነውም ብለዋል፡፡ ሰልጣኖች ለዚህ ስራ እራሳቹን እያዘጋጃቹሁ በስራቹሁ ስኬታማ በመሆን ለማህበረስብ የሚተረፍ ፕረጀክቶችን በመንደፍ እንድትበረቱ ስል አቶ ደምሴ ባቲ ገልዋል፡፡

ወ/ሮ ንጋቷ መኮንን የነጌ ተስፋ የራስ አገዝ ቡድኖች ማህበራት ጥምረት ስራ አስኪያጅ ጥምረታችን ሰፍ ስራዎችን እየሰራ ነው፡፡ አሁን ወደ ድርጅት አደገናል፡፡ ህጋዊ ፈቃድ ማለትም የራሳችን ማንነት የሚገልጽ ሰርትፍኬት ከመንግስት አግኝተናል፡፡ አሁን በሁለንተናዊ መልኩ እራሳችን እያበቀን እና እያደራጀን በራሳችን ለራሳችን እና ለማህበረሰባችን ብልጽግና የምንሰራበት ጊዜ ደረሷል፡፡ እየተደገፍን ብቻ ሳይሆን በአጋረነት ከተለያዮ አካለት ጋረ እንሰራለን፡፡ ለዚህ ሁሉ ቅደመ ዝግጅት እያደረግን ነው ስሉ ወ/ሮ ንጋቷ ገጽዋል፡፡
#ShareTrust #EKHCHADC #YenegeTesfa

Add a Comment