ቀ

የልጆችና ወላጆች ሳምንት በተለያየ መረሃ ግብር በአዲሎ መከበሩ ተገለጽ

የልጆችና ወላጆች ሳምንት በተለያየ መረሃ ግብር በአዲሎ መከበሩን የኢትዮጵያ  ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን የአዳሎ ከተማ ቁጥር 2 ቃለ ሕይወት የልጆች ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡

የልጆች እና ወላጆች ሳምንት ታህሳስ 7፣8፣9 ፣10 እና 12 ላይ የተለያዮ መረሃ ግብሮችን በማድረግ የተከበረ ሲሆን ከመረሃ ግብሮችም መካከል ለወላጆች በልጆች ጥበቃ ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና፣ሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳት ዘመቻ፣ በልጆች ጥበቃ ዙሪያ ለሚመለከታቸው ለመንግሥት አካለት እና ለሀይማኖት ተቋማት ስልጠና መስጠት እና የልጆች ጥበቃ ዙሪያ ለከተማው ማህበርስብ  ግንዛቤ ለመፍጠር ያለማ የጎዳና የማህበረሰብ ሩጫ በማድርግ ተከናውኗል፡፡

በመረሃ ግብሩም ልጆች የነገ አገር ተረካቢ ብሎም  የቤተሰብ ተስፋና ስጦታ በመሆናቸው የመታወቅ፣ የመጠበቅና የመወደድ መብታቸው  ሊጠበቅ  እንደሚገባ የኢትዮጵያ  ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን የአዳሎ ከተማ ቁጥር 2 ቃለ ሕይወት የልጆች ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለፀ። ፕሮጀክቱም በኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የሚደገፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

“እያንዳንዱ ልጅ ሊታወቅ ሊወደድ እና ሊጠበቅ ይገባል በሚል መሪ ቃል የልጆችና ወላጆች ሳምንት  በደማቅ ተከብሯል ።

ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ “እያንዳንዱ ልጅ ሊታወቅ ፣ ሊወደድና ሊጠበቅ ይገባል” በሚል መሪ ቃል በአዲሎ ከተማ ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየው የልጆችና የወላጆች ሳምንት ክብረ በዓል በትናንትነው ዕለት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ተጠናቋል ።

በማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የአጋርነት አሳላጭ አቶ ዓለምሰገድ ግርማ እንደተናገሩት የፕሮግራሙ ዓላማ ወላጆች በልጆች ዕድገት ላይ ድርሻቸው የጎላ በመሆኑ ለማበረታታት እና ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ክብረ በዓል ነው ብለዋል ።

ቤተሰብ በልጆች ዕድገት እና የህይወት ዑደት ላይ የራሱን በጎ ተጽእኖ ማሳረፍ ይችላል ያሉት አቶ ዓለምሰገድ የልጆችን ሁለንተናዊ አካላዊ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ፍላጎት እንዲጠበቅ ወላጆችና አሳዳጊዎች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል ።

የአዲሎ ቁጥር 2(ሁለት) ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የልጆች ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ፈቃዱ ተስፋዬ በበኩላቸው ማስተባበሪያው ከልጆች ልማት በተጨማሪ ሌሎች አካላትን በማስተባበር አቅመ የሌላቸው ወገኖች ቤት ግንባታ እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል ።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ ልጅተ ተኮር ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ የቤተሰብ ኑሮ ካልተሻሻለ ለአንድ ልጅ ብቻ በሚደረግ ድጋፍ  ከተረጂነት መውጣት የማይቻል በመሆኑ ወላጆች በማህበር ተራጅተው በመቆጠብ ሀብት ማፍራት እንዲችሉ ፕሮጀክቱ ተግባሩን ማህበረሰብ ተኮር በማድረግ የወላጆችን ኢኮኖሚ ለማሻሻልም በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል ።

የአዲሎ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ባይዳ ጃተኖ በበኩላቸው ህጻናት ታውቀው ተወደውና ተጠብቀው የማደግ መብታቸውን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትብብር እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

የነገ አገር ተረካቢ በሆኑ ህጻናት ጉዳይ ላይ ሁሉም የየራሱን ሚና መወጣት አለበት ያሉት ወይዘሮ ባይዳ ወላጆችና አሳዳጊዎች ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

በመርሐ-ግብሩ የአዲሎ ዙሪያ ነዋሪዎች የአዲሎ ከተማ ነዋሪዎች የአዲሎ ከተማ ቁ-2 ቃለ ህይወት ቤተ-ክርስቲያን አባላት የፕሮጀክቱ ሀላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱ የህፃናት ፣ የወንዶችና  የሴቶች የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በማካሄድ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ እና የገንዘብ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *