አዳማ፡- የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በኮሚሽኑ አሰተባባረነት እና በአዳማ ከተማ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ማህበራት ህብረት ጥምረት ፈጻሚነት የሚተገበር ለሶስት ዓመት የሚቆይ የማህበርሰብ ተኮር የልማት ፕሮጀክት በ1.5 ሚሊዮን ዶላረ ህዳር 14/03/2017 ዓ.ም አጋረ አካላት፣ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኘበት በይፋ በአዳማ ከተማ ሮቢ ሆቴል አስጀመሮል፡፡
የፕሮጀክቱን በይፋ መጀመር በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬ ለለፉት 20 ዓመታት የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ማህበራት ህብረት ጥምረት ስያደራጅ፣ ሲደግፍ እና እራሱን ችሎ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ እንድቀሳቀስ ለማድረግ በረካታ ድጋፎችን ኮሚሽኑ ሲያደረግ ነበረ ያሉ ሲሆን በዝህም ጥረት ቡድኑ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ህጋዊ ሰውነት እና እውቅና እድያገኝ ተደረጎል፡፡


ይህ ዛሬ የሚናሰጀምረው ማህበርሰብ ተኮር ፕሮጀክት ለለፉት 20 ዓመታት የተደከመበት እና ዋጋ የተከፈለበት የስራ ውጤት ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ፕሮጀክቱ በዋናነት አሁንም የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረቶችን ራሳቸውን እንድችሉ፣ በራሳቸው እንድንቀሳቀሱ እና የበቃ ተቋሟዊ አወቃቃር እና አቅም እንድያጠናክሩ የሚያስችል ውጥን የያዘ ሲሆን ማህበረሰብ ተኮር ሆኑ የልማት ስራዎችን መስራት እንዲችሉ በማስቻል ለማህበረሰብ እና ለአገር ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋኦ እንዲያበረክቱ ማድረግ ነው፡፡
ይህንን ፕሮጀክት የሚደግፉ አጋረ አካለትም The Share Trust, Warande Advisory Centre (WAC) እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ሲሆኑ ፕሮጀክቱን በይፋ በማስጀመረ ፕሮግራም ላይ የተገኘት የዋራንዴ አዲቫዜሪ ማዕከል መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ችላንዴ ኩሎባ-ዋሪያ በበኩሎ ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን እና የነጌ ተስፋ ራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረቶች ጋረ በአጋሪነት መስራት መጀመራቸው መልካም እና በቦጎ አይን እንደሚመለከቱን ገልጽዋል፡፡ በፕሮጀክት ማስጀመሪያ መሪሃ ግብር ላይ እንደተናገሩት ትክክለኛ መሪነት ትዕዛዝ መስጠት እና ማውረድ ሳይሆን ለማህበረሰብ ችግሮች ማህበረሰብ ተኮር መፍቴሔ ማምጣት ነው፡፡ እራሳችን ነቅተን የማህበረሰባችን አቅም ከልገነባን በስተቀር ከውጭ በሚገኝ እረዳታዎች ብቻ ዘላቂ እና ቀጣይነት ያለውን ልማት እና ዕድገት ማምጣት አይቻልም ብለዋል፡፡




ነገረ ግን ይህ ፕሮጀክተ የማህበረሰብ ልማት እና ዕድገት ቀጣይነት እንድኖረ በማህበርስብ መረ እና ተኮር የልማት ስራዎች ላይ በትኩረት እና በጥልቀት ይሰራል፡፡ ግለሰቦች፣ ማህበሶቦች እና እንዲሁም የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረቶች እራሳቸውን ችለው እና ለማህበረሰብ ተረፈው ለማየት በትጋት ማህበረስብ ተኮረ ስራዎች ላይ መስራት ለነጌ ማይባል የዕለት ዕለት ተግባራችን መሆን አለበት ስሉ ገልጽዋል፡፡ ይህም ማህበረሰብ ተኮረ የልማት ስራ እንቅስቃሴ አዳማ ተጀምሮ አዳማ የሚቆሚ ሳይሆን ወደ ሌሎች ክልሎች እና አገራት መስፋፋት በሚችል ሁኔታ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ችላንዴ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ለዝህ የሚሆን አቅም፣ሀብት እና ሊሰራ የሚችል የሰው ኃይል እና ምቹ ሁኔታዎች አሉ ብለዋል፡፡
የአዳማ ከተማ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምሮቶች ራስን ለመቻል የሚያስችል ወሳኝ የለውጥ መሳሪያ ነው የተባለ ሲሆን ጠንካራ የአዳማ ከተማ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረቶች ማጠናከር ለግለስብ፣ ለማህበርሰብ እና ለአገር ዕድገት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡
ስራን ለመፍጠር፣ ኢኮኖሚውን ለማጎልበት እና ድህነት ለመቀነስ የራስ አገዝ ቡድን የስራ እንቅስቃሴ እና ጥምረት ወሳኝ መሆን በስብሳበው ተገልጾል፡፡ የራስ አገዝ ቡድንኖቹ በተለያዮ የስራ ዘርፎች ለመስራት በዘጋጁት የስራ ዕቅድ ላይ የተወያዮ ሲሆን የራስ አገዝ ቡድኖችም የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻያ፣ በጤና፣በትምህርት እና አቅም ግንባታ፣ ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ሲሆን ይህም አካል ጉዳተኞችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና ልጆችን ተጠቃሚ እና ቀዳሚ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ለአብነትም የስራ ዕቅዳቸውን ከቀረቡት የራስ አገዝ ቡድኞች ጥምሮቶች መካከል ነህሚያ ፣ትንሳኤ እና ፋረስ ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ጥምረቶች በስራቸው 273 የራስ አገዝ ቡድኖች እና 27 የማህበራት ሕብርቶች አሎቸው፡፡
ይህም ማህበርሰብን የማብቃት ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ ከኦሮሚያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ፣ከኦሮሚያ ሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ፣ከኦሮሚያ ስራ ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ፣የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ፣የኦሮሚያ ጤና ቢሮ፣ ከኦሮሚያ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ እንዲሁም የአዳማ ከተማ ፋይናንስ ጸ/ቤት ፣የአዳማ ከተማ ጤና ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ ሴቶች ፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ የስራ ፈጠራ እና ክህሎት ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ተወካዮች በተገኙበት በይፋ የማስጀመር መረሃ ግብር ተከናውኖል፡፡
ፕሮጀክቱም ለምቀጥሉት የሶስት ዓመት የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻያ፣ በጤና፣በትምህርት እና አቅም ግንባታ ዙሪያ በትጋት በመስራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው በለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እና በቅንጂት የሚተገበር ይሆናል፡፡
የራስ አገዝ ቡድኖች እና ጥምረቶችን ከማድራጀት አንስቶ አሁን እሰከ ደረሱበት ሁለንተናዊ የዕድገት ደረጃ ለለፉት 20 ዓመታት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ከፍተኛ አስተዋጾኦ ያደረገ ስሆን አሁንም ማህበረሰብን እና ፍጥረትን ሁሉ በክርስቶስ ልብ ማገልገልን መሪ ቃሉ አድረጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

አቶ ድንቁ ሹሚ በህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ እና አደጋ መከላከል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩሉ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ማህበራት ህብረት ጥምረት ዛሬ ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሸን ከፍተኛ ድጋፍ እና ጥረት አድርጓል ። የልማት ኮሚሽኑ የሁለት አስርት ዓመታት ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ክትትል ዛሬ ይህን ጠንካራ የነጌ ተስፋ የራስ አገዝ ጥምረቶችን ለአዳማ ከተማ ማህበረሰብ መወለድ ችሎል። ይህ ስኬት ለኮሚሽኑ ይሁን ለኦሮሚ ክልል በተለይም ለአደማ ማህበረሰብ ትልቅ ስኬት ነው። ይህ ዛሬ ያስጀመረነው ፕሮጀክትም እንደ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ እና አደጋ መከላከል ፕሮግራም ከሚተግብራቸው እና ከሚያስተባብራቸው በርካታ የፕሮጀክት ስራወች መካከል አንዱ ነው ስሉ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ላይ የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ማህበራት ህብረት ጥምረት እራሳቸውን የቻሉ ተቋም ለመሆን ጉዞ ጀምረዋል። ይህንንም እንደሚያሳኩት በጥምረቶቹ እምነት አለን። ይህም እዉን እንዲሆን ኮሚሽኑ የማስተባበር ሚናውን በብቃት እንደ ቀደመው በከፍተኛ ሀላፊነት ይወጣል ብለዋል።
በኮሚሽኑ የዚህ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ እንዳለ ወ/ሳማያት ጥምረቶቹን ግብ ለማሳካት እና ውጤታማ እንዲሆኑ በየግዜው ክፍተቶቻቸወን በመለየት የአቅም ግንቦት ሲልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም ወ/ሮ ንጋቷ መኮንን የነገ ተስፋ የራስ አገዝ ማህበራት ህብረት ጥምረት ስራ አስኪያጂ ደግሞ እኛ ተረጂነትን አንፈልግም ሰርቶ ጥሮ መለውጥን እንጂ ለዝህ ማሳያ ደግሞ በተሰጠን ድጋፍ እና አቅም ግንባታ በለፉት ዓመታት እራሳችንን እየለወጥን ለማህበረሰባችንም ለውጥ የበኩላችንን እያበረከትን እንገኛለን ብለዋል፡፡ አሁንም በያዝነው ዕቅድ መሰረት በጥረት ወደ ስኬት እንደረሳለን በቁጣበችንም ነጌያችንን የተሸለ እናደረጋለን ስሉ ወ/ሮ ንጋት ገልጾዋል፡፡
በይፋው ማስጀመሪያ መሪሃ ግብረ የተገኙ የተለያዮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ለዚህ ፕሮጀክት ሲኬት በሚያስፈልግ ሁሉ ድጋፍ እንዴሚያደረጉ ገልጽው እስከአሁን ድርስ ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ስለሚገኙ የተለያዮ የልማት ስራዎች እና ቱረፋቶች ኮሚሽኑን እና አጋር አካለትን አመስግነዋል፡፡
አሁን ላይ የራስ አገዝ ጠቅላላ ቁጠባ 46.3 ሚሊዮን የደረሰ ስሆን አጠቃላይ ከፕታላቸው 83.5 ሚሊዮን መድረሱ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Add a Comment