በውይይቱም የራስ አገዝ ቡድኞች የስራ እንቅስቃሴን የሚደግፉ አጋር አካለት ማለትም The Share Trust, Warande Advisory Centre (WAC)፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን እና የራስ አገዝ ቡድኞች አስተባበሪዎች የተገኙ ስሆን የአዳማ ከተማ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምሮቶች ባዘጋጁት የስራ ዕቅድ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደረጎል፡፡






አዳማ፡- የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን አጋር አካላት እና የአዳማ ከተማ የራስ አገዝ ጥምረት ስራ ለመስራት የሚያስችል የስራ ዕቅድ ላይ በአዳማ ከተማ ሮቢ ሆቴል ውይይት አደረጉ፡፡




የአዳማ ከተማ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምሮቶች ራስን ለመቻል የሚያስችል ወሳኝ የለውጥ መሳሪያ ነው የተባለ ሲሆን ጠንካራ የአዳማ ከተማ የራስ አገዝ ቡድኖች ጥምረቶች ማጠናከር ለግለስብ፣ ለማህበርሰብ እና ለአገር ዕድገት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡
ስራን ለመፍጠር፣ ኢኮኖሚውን ለማጎልበት እና ድህነት ለመቀነስ የራስ አገዝ ቡድን የስራ እንቅስቃሴ እና ጥምረት ወሳኝ መሆን በስብሳበው ተገልጾል፡፡ የራስ አገዝ ቡድንኖቹ በተለያዮ የስራ ዘርፎች ለመስራት በዘጋጁት የስራ ዕቅድ ላይ የተወያዮ ሲሆን የራስ አገዝ ቡድኖችም የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻያ፣ በጤና፣በትምህርት እና አቅም ግንባታ፣ ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ሲሆን ይህም አካል ጉዳተኞችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና ልጆችን ተጠቃሚ እና ቀዳሚ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ለአብነትም የስራ ዕቅዳቸውን ከቀረቡት የራስ አገዝ ቡድኞች ጥምሮቶች መካከል ነህሚያ ፣ትንሳኤ እና ፋረስ ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ጥምረቶች በስራቸው 273 የራስ አገዝ ቡድኖች እና 27 የማህበራት ሕብርቶች አሎቸው፡፡
በነጌው ዕለትም ማህበርሰብን የማብቃት ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ ከኦሮሚያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ፣ከኦሮሚያ ሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ፣ከኦሮሚያ ስራ ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ፣የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ፣የኦሮሚያ ጤና ቢሮ፣ ከኦሮሚያ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ እንዲሁም የአዳማ ከተማ ፋይናንስ ጸ/ቤት ፣የአዳማ ከተማ ጤና ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ ሴቶች ፣ ሕጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ የስራ ፈጠራ እና ክህሎት ጽ/ቤት፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ተወካዮች በተገኙበት በይፋ የማስጀመር መረሃ ግብር ይደረጋል፡፡
ፕሮጀክቱም ለምቀጥሉት የሶስት ዓመት የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻያ፣ በጤና፣በትምህርት እና አቅም ግንባታ ዙሪያ በትጋት በመስራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው በለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እና በቅንጂት የሚተገበር ይሆናል፡፡
የራስ አገዝ ቡድኖች እና ጥምረቶችን ከማድራጀት አንስቶ አሁን እሰከ ደረሱበት ሁለንተናዊ የዕድገት ደረጃ ለለፉት 20 ዓመታት የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ከፍተኛ አስተዋጾኦ ያደረገ ስሆን አሁንም ማህበረሰብን እና ፍጥረትን ሁሉ በክርስቶስ ልብ ማገልገልን መሪ ቃሉ አድረጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

Add a Comment