zz

ጂስራ የሠላም፣የፍቅር፣የአብሮነት እና ግጭት መፍቻ ድልድይ ሆኖ አላማውን እያሳካ ነው፡

ጂስራ የሠላም፣የፍቅር፣የአብሮነት እና ግጭት መፍቻ ድልድይ ሆኖ አላማውን እያሳካ ነው፡ አቶ እንዳለ ወ/ሳማያት

  • ልማት ኮሚሽኑ እያካሄደ የነበረው ሰላም ላይ ትኩርት ያደረገ ምክክር ወርክ ሾፕ ተጠናቀቀ፡፡

ልማት ኮሚሽኑ ሰኔ 5/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል  ያካሄደዉ  በሰላም ላይ ትኩርት ያደረገ ምክክር ወርክ ሾፕ ስኬታማ እንደነበረ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ጂስራን ከሁሉም ቤተ እምነቶች በጋራ በመሆን ፕሮጀክቱን አላማ ለማሳካት እየሰራን ነዉ ያሉት አቶ እንዳለ እንደ ቃለ ሕይወት እንድንሠራ በተሰጡ አከባቢዎች ቦጎ ተጽዕኖዎችን ማምጣት ተችሎል ብለዋል፡፡

በምዕራብ አርሲ፤ሻሽመኔ ከተማ፣አዋሳ አከባቢ፤ዶሬ ሻማና አከባቢ፣በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ፣ በሀላባ ዞን ሀላባ ከተማ እና ሌሎች አከባቢዎች ልማት ኮሚሽኑ የጋራ ተነሳሽነት ለስልታዊ ሀይማኖታዊ ተግባር(ጂስራ) ፕሮጀክት ሁሉም ሀይማኖቶች እና ማህበረሰቡ ለጋራ ሠላም፣መከባበርና መቻቻል በመካካላቸው እንዲሰፍን በስፋት እና በጥልቀት እየሰራን ነው፡፡ እነዚህ አከባቢዎች እንደሚታወቀው ከአሁን በፍት ግጭቶች የሚበዙባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን በፕሮጀክቱ እና ባለድርሻ አካላት በተሰሩ የሠላም ግንባታ ስራዎች ሠላምን መያዝ፣መጠበቅ፣ለሠላም መስራት እና ሠላምን ማጽናት ከበፊቱ እየተጠበቀ መጥቶል፡፡ ይህ ፕሮጀክት የሀይማኖት አባቶችን፣የአገር ሽማግሌዎን፣አባ ገዳዎችን፣የመንግስት አካለት፣ወጣቶችን እና ሴቶችን እንደ ድልድይ ሆኖ የማገናኘት ስራ በስፋት በመስራቱ አሁን ላይ ከስጋት በተሻለ  አከባቢው ሠላማዊ ሆኗል ስጋቶች ሙሉ በሙሉ ባይጠፉም፡፡

የተጣሉቱ ተረቀዋል፣የተራራቁቱ ተቀራረበዋል፣ለሰላም ስጋት የሆኑቱ የሠላም መሳሪያ ሁነዋል፡፡ በአጠቃላይ ሰላምን፣ልማትን፣ በቤተ-እምነቶች ዘንድ መቀራረብን፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች ተጠናክረው በመቀጠላቸው አሁን ከስጋት ይልቅ የሠላም አማራጮች በሁሉም ዘንድ ቅድሚያ የሚሰጥ ሁኖል፡፡ ይህም የሆነው በልማት ኮሚሽኑ በኩል ጂስራ ፕሮጀክት በፈጠረው የግንዛቤ እና የምክክር መድረኮች፣ ስልጠናዎች እና ትምህርቶች የተነሳ ነው፡፡

በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የሀይማኖት ተቋም ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ፓስተር ዳንኤል ጥላሁን የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በጂስራ ፕሮጀክት እየሰራ ያለው የሠላም ግንባታ ስራዎች በአከባቢያቸው ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ እንደለ  ገልጸዋል፡፡ በሲዳማ  እና በኦሮሚያ ክልል  ድንበር ላይ  ከአራት ወረዳዎች ጋር እንገናኛለን ያሉት ፓስተር ደንኤል ፣ ጅስራ ለአገር ሽማግሌዎች፣ለሀይማኖት አባቶች፣ እርቅ ላይ ለሚሰሩ ለመንግስት አካላት በሙያ የተደገፈ ትምህርት እና ስልጠና  በመስጠቱ የነበረው ባህላዊ የእርቅ ስርዓት አቅም እንዲያገኝ እና ትልቅ ለውጥ በአከባቢው  እንዲያመጣ አድረጎል፡፡

በፊት በአከባቢያችን ብዙ ችግሮች ነበሩ፡፡ በአከባቢው በቆሎ በብዛት ይመረታል ነገረ ግን ሲዘራ እና ምርት ሲሰበሰብ በሚፈጠረው ግጭቶች ብዙ ሰው ከሁሉም ወገን  ይሞት ነበረ፡፡ ይህም ግጭት የቆየ ግጭት ነው ያሉት ፓስተር ድንኤል ጀስራ ከመጣ በኃላ ብዙ ለውጥ አለ፡፡ የአገረ ሽማግሌዎች ከኦሮሚያና፣ ከሲዳማ ክልል በአንድ ላይ ለችግሩ መፍትሔ ላይ እየመከሩ  ከጂስራ ባገኙት ሙያዊ ድጋፍ፣ ትምህርት እና ስልጠና ችግሩ የሚፈታበትን ስልት ነድፈው በመንቀሳቀሳቸው በአከባቢው ላይ ትልቅ ለውጥ መጥቷል፡፡ አሁን ሞት ቆሟል፡፡ የብዙዎችን ሕይወት የሚቀጥፍ ግጭት የለም፡፡ ያው አልፎ አልፎ በግጦሽ መሬት ግጭቶች ቢኖሩም እንደ በፊቱ አይደለም ያሉት ፓስተር ዳንኤል እንደ ሀይማኖት አባት ከስልጠናው ያገኘነውን ትምህርት እና ልምድ ወደ ማህበረሰቡ ወርደን  እያስተማርን አሁን ላይ ማህበርሰባችንም ስለ ሠላም ግንዛቤው እያደገ ነው፡፡

 ግጭቶችንም በሠላማዊ መንገድ መፍታት እየተለመደ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ለውጥ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ጂስራ ፕሮጀክት ከእኛ አካባቢ በዘለለ በሌሎች አከባቢዎችም ትልቅ ለውጥ እያመጣ ስለሆነ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን እና ልማት ኮሚሽን በህዝብ እና በአገር ልማት እንዲሁም በሰዎች የግንዛቤ ለውጥ እና ግጭት ባለባቸው ቦታዎች ላይ የምትሰራውን  ስራ አጠናክራ እንድትቀጥል ሲል ፓስተር ዳንኤል ገልጾል፡፡

በዕምነትና ሀይማኖት ነጻነት ጽንፈኝነትን መከላከል፣በሰላም በአብሮነት መኖር እና አገራዊ የግጭት አፈታትን በማጠናከር ረገድ የተሰጠው ስልጠና እና የምክክር መድረክ ጥሩ ልምድ ያገኘንበት ነው ያሉት ፓስተር ዳንኤል በዕምነትና ሀይማኖት ነጻነት ጽንፈኝነትን ለመከላከል፣በሰላም በአብሮነት መኖር እና አገራዊ ግጭቶችን በተገቢው ሁኔታ መፈታት እንዲንችል የሚያስችል ልምድ እና ትምህርት መቅሰማቸውን ገልጸዋል፡፡

ጋራድ ሀሰን ቀሪቾ የሀላባ ዞን የአካባቢ ሽማግሌ ሲሆኑ በአካባቢ ሠላም ዙሪያ የሚሰሩ አባት ናቸው፡፡ በሠላም ዙሪያ ብቻችንን አይደለም የምንሰራው፡ ሁሉም የሚመለከተው አካል ይሳተፋል፡፡ ሁሉም ለሠላም ከሰራ ሠላም ይሆናል ይላሉ ጋራድ ሀሰን ቀሪቾ፡፡ ሀላባ ላይ ሠላም የሆነው ሁሉም ለሠላም ግድ የሚላቸው አካላት በቅረበት እና በመቀባበል ስለ ሰራን ነው ብለዋል፡፡

ግጭቶች ከመፈጠራቸው በፊት ሊነሱ የሚችሉባቸውን ምክንያቶች ለይተን በማወቅ በዚያ ላይ እየሰራን ግጭቶችን በአካባቢያችን እንደይፈጠር እያደረግን እንገኛለን ያሉት ጋራድ ሀሰን በቂ የመረጃ ልውውጥ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር እንለዋዋጣለን፣ጫካ ሳይገቡ ማህበረሰቡን ጫካ አድረገው ግጭትን የሚፈጥሩትን በመለየት በሚደርሰን መረጃ መሰረት ወደ ሠለም እንዲመጡ እንሰራለን ፡፡

በፊት አንድ አንድ የሀይማኖት ግጭቶች በተላይ ሀይማኖታዊ በዓሎች ሲኖሩ አልፎ አልፎ በሀላባ ይነሱ ነበረ ነገር ግን ከጂስራ ጋር መስራት ከጀመረን በኃላ ከሁሉም ሀይማኖቶች ጋር ሠላማዊ ግንኘነት ተፈጥሮል ያሉት ጋራድ ሀሰን ቀሪቾ አሁን ላይ በልማት ኮሚሽኑ ጂስራ ፕሮጀክት ትምህርት እና ስልጠና ባገኘነው ልምድ ፕሮቴሰታንቱ እኛን/ሙስሊሙን ይጠብቃል፡ እኛም/ሙስሊሞች እነሱን እንጠብቃለን፤ኦርቶደክሱ እኛን/ሙስሊሞችን  ይጠብቃል እኛም/ሙስሊሙሞች  ኦሮቶዶክሶችን እንጠብቃለን፡፡ ለምን ካላቹሁ አገር የጋራ ነው ሀይማኖት የግል ነው፡፡በጋራ አገር በሠላም መኖረ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው፡፡ ከጂስራ ከተገናኘን ወዲህ ሰው ከስጋት ነጻ ነው፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *