photo_2023-04-06_23-49-47

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው
የቤተ ክርስቲያናችን 62ተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ከመጋቢት 28 – 29 2015 ዓ.ም በቤተ ክርስቲያናችን ደቡብ ምዕራብ ቀጣና አስተናጋጅነት በቀጣናው ጽሕፈት ቤት መገኛ አርባ ምንጭ መካሄድ የጀመር ስሆን በእለቱም ርፖርቶች የቀረበው ሰፍ ውይይቶች ተደርጎል፡፡
62ተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ አገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባዔ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር፣ የጋሞ ዞን አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ፕርዝደንት፣ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቦርድ አባላት እና ሁሉም እንግዶች በተገኙበት በጸሎት፣ በአምልኮና የእግዝአብሐርን ቃል በመካፈል የተጀመረ ሰሆን በዛሬው እለት በቀረቡ በተለያዮ ርፖርቶች ላይም ውይየይት ተደረጎል፡፡
››ጉባዔው የቤተ ክርስቲያኒቱ ወደ መቶኛ ዓመት በእጥፍ እድገት መሸጋገሪያ ስልታዊ ዕቅድ የአንድ ዓመት አፈጻጸም የሚገመገምበት እና ሪፖርት የሚቀርብበት፣ የአዳዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀቶች ይኸውም የቀጣና እና ኀብረቶች ማጽደቅ የሚከናወንበት ብሎም የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጸሐፊ እና የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ምርጫ የሚደረግበት እና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልዩ ልዩ ብሔራዊ አጀንዳዎች የሚቀርቡበት እና በጉባዔው ውሳኔ የሚሰጥባቸው ይሆናል፡፡›› በጉባዔው ላይ ከመላ አገሪቱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በኅብረቶቻቸው አማካኝነት የተወከሉ የጉባዔው አባል የሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች በቦታው በመገኘት በጉባዔውን አየተሳተፉ ነው፡፡ ጉባዔው መጋቢት 27 ምሽት እንግዶችን በመቀበል የጀመር ሲሆን ዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *