p

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤው ሹመቶችን አፀደቀ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤው ሹመቶችን አፀደቀ
በቀረቡ አገር አቀፍ የቤተክርስቲያንቱ አጀንዳዎች ላይ ዉሳኔም አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባዔ ሹመቶችን አፀድቆ በተለያዩ በቀርቡ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ጉባኤው የቤተክርስቲያንቱን የዋና ጺ/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ስምዖን ሙላትን በዲጋሜ የመረጠ ስሆን የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በተመለከተ ጉባዔዉ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ታሎሬን በዲጋሜ የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ እንድቀጥሉ መርጦል። ከዚህ በተጨማሪ በጎዳሉት ቦርድ አባል ቦታ የማሟላት ምርጫ ተደርጎአል።
ጉባኤው ለተመረጡቱ መልካም የስራና የአገልግሎት ግዜ እንዲሆንላቸው ፀሎት እና ቡራኬ አድርጎላቸዋል። ለ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባዔም አድስ አበባ እና አከባቢዋ ቀጠና እንድንሆን ተወስኗል። የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ጥቀስ “እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤” ሚለውን መሪ ጥቅስ ሁኖ ፀድቆል።
— ቆላስይስ 1፥28
የቤተክርስቲኒቱ መቶኛ አመት 2020 ዓ.ም ለማክበር ተወስኗል። 100ቶኛ አመት በተመለከተ ስራዎችን የሚሰሩና ሚያስተባብር አብይ ኮሚቴም ተመርጠዋል።
ጉባኤው በአንድነት የጌታን እራት በመወሰድ ተጠናቋል።

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *