የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን የጋራ ቦርድ ስብሰባ በትናንትና ዕለት ተደረገ፡፡ ስብሳባው በጸሎትና እግዚአብሔርን ቃል በመካፈል የተጀመረ ሲሆን በሚከተሉት የዕለቱ አጀንዳዎች ላይም ጥልቅ ውይይት በማድረግ አስፈለጊ የሆኑ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎችን ቦርዱ አስቀምጦል፡፡
በዕለቱ የነበሩ አጀንዳዎች፡- አዲስ የቦርድ አባላት መቀበልና ሽኝት፣ያለፈውን ቃለ ጉባኤ በማንበብ ከቃለ ጉባኤ የሚነሱ ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ ማጽደቅ፣የልማት ኮሚሽን ማናጅመንት መዋቅርና የደመወዝ ስኬል ስለመከለስ/ ማሻሻል፣ የቤ/ክ የልማት ኮሚሽን ቅንጅታዊ አሠራር መመሪያ ተነጋግሮ ማጽደቅ ፣ ቅንጅታዊ ማኑዋል አተገባበር፤ የሃብት አሰባሰብ እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ጉዳይ በሚመለከት፣ አስቸኳይና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን አይተው ለቦርድ ውሳኔ የሚያቀርቡ ከልማት ቦርድ አባላት ውስጥ ኮሚቴ መሰየም የዕለቱ ስብሰባ አጀንዳዎች ሲሆኑ ቡርዱም በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት አቅጣጫዎችን እቀምጦል፡፡
Add a Comment