vc

ኮሚሽኑ የ2 ዓመት ግማሽ የስራ አፈጻጸምና የኮሚሽኑን ስልታዊ ዕቅድ(Strategic Plan) ግምገማ አከሄደ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን የሁለት ዓመት ግማሽ የስራ አፈጻጸምና ስልታዊ ዕቅድ(Strategic Plan) አፈጻጸም ግምገማ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም በልማት ኮሚሽኑ ጽ/ቤት አካህዶል፡፡

በግምገመው መክፈቻ ንግግር ያደረጉቱ የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተፈራ ተሎሬ(ፕኤችዲ/PhD) ኮሚሽኑ በእግዝአብሔር እርዳታ በለፉት ዓመታት የተዘጋጅውን ስልታዊ ዕቅድ በመከተል በርካታ ስኬታማ ስራዎችን መከወን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ 2021-2025 Strategic Plan አዘጋጅቶ እየተገበር የሚገኝ ስሆን በአሁኑ ሰዓትም የሁለት ዓመት ግማሽ ድርስ ያለውን አፈጻጸም በአድስ አበባ በልማት ኮሚሽኑ ጽ/ቤት ገምግሞል፡፡ ግምገመው ያለፉትን ዓመታት አፈጻጸምና ለቀሪው 2 ዓመት ግማሽ የስራ ግዜም አስፈላግ የሆኑ ግባዓቶችን በመውሰድና አቅጣጫ በመያዝ  ግምገማው ተደርጎል፡፡

ሁሉም መምሪያዎች እስካሁን በStrategic Plan መሰረት የየራሳቸውን የስራ ጉዞ በግምገመው ላይ ያቀርቡ ስሆን የ5ት ዓመቱን Strategic Plan መሰርትም መሻሻል፣መጨመር ያለባቸው ነገሮች ከዓለም አቀፍ፣አገር አቀፍ ፖሎቲካዊ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ዲርጅታዊ ሁኔታ በማገናዘብ ግብዓቶችን ተውስደውና ለተሸለ አፍጻጸም አቅጣጫ መያዝ የሚያስችሉ ነገሮች የተደሰሰበት ሁነት ስሆን፡ ከዝህ ግምገማ በመቀጠልም ልማት ኮሚሽኑ በሰበሰባቸው ግብዓቶችና እ.ኤ.አ 2021-2025 Strategic Plan ላይና በቀሪው የስራ ዓመታት ዙሪያ ሌላ የተጠናከርና ከፍ ያለ ውይይቶችን እና ግምገማወችን ከኮሚሽኑ የበላይ አመራሮች/ቦርድ እና ኃላፊዎች ጋር እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ኮሚሽኑ በሁለት ዓመት ግማሽ የስራ አፈጻጸምም 1,053,192,388.063 ብር በስራ ላይ ያዋለ ስሆን ከ1 ሚሊየን በላይ የሆኑ ሰዎችን በወሃ፣ በትምህርት፣ በጤና እና በላይቨሊሁድና ሪዝሊያንስ መምሪያዎች በተሰሩ ዘረፍ ብዙ ስራዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በግምገመው ተደምጦል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *