IMG_8579

ኮሚሽኑ በድጂታል ሴፍቲና ድህንነት ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ያተኮር ስልጠና ለሰራተኞቹ ሰጠ

አጋር ድርጅታችን ብሬድፎርዘዎርልድ በኬኒያ ናይሮቢ ያዘጋጀውን የአንድ /1/ ሳምንት ስልጠና ተከትሎ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በድጂታል ሴፍቲና ሴኩሪት/ድህንነት ላይ ያተኮር ስልጠና ለሰራተኞቹ በኮሚሽኑ ጽ/ቤት በጥቅምት 13/2016 ሰጥቶል፡፡

ስልጠናው አላማ በስራ ቦታ በድርጂቱ እና በሰራተኞች ላይ ሊቃጣ የሚችሉ ድጂታል ጥቃቶችን ለመከላከል የሚረዳ ስልጠና ስሆን ኮሚሽኑም ይህን ስልጠና ሰራተኞችን በቡድን ከፋፍሎ መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ተሎሬ ገልጸው ቀጣይ ቡድንም በሚቀጥሉት ግዜ ስልጠናውን እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡

በድጂታል ሴፍቲና ሴኩሪት/ድህንነት በተመለከተ በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት እና የተግባር ልምምዶችም የተደረገበት ውጤታማ ስልጠና ነበር፡፡ ስልጠናውም በኢትየጵያ ወንጌላት መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን አይቲ ክፍል ኃላፊ  በሆነው  አቶ በርከት ካሳየ  ነው የተሰጠው፡፡

አለም ያፈራቻቸውን የዲጂታል መሰሪያዎችን መጠቀም ጥቅም እንደለው ሁሉ አስፋጊ የሆኑ ጥንቃቄዎች ከልተደረጉ ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ በስልጠነው ያመለከተ ስሆን ሰራተኞች በዲርጂቱ በምስሩ ስራቸውም ሆነ የግል ጉዳያቸው ድህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ማድረግ ስላለበቸው ጥንቀቄዎች ተግባር የታከለበት ስልጠና ሰጥቶል፡፡

በኮሚሽኑ የላይቨሊሁድ እና ሪዚሊያንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዲንቁ ሹሚ ይህን ስልጠና ለመጀመሪያ ግዜ ኬንያ ከአቶ ኪዳን ቴኒ ጋር መሰልጠናቸውን ገልጽው ለኮሚሽኑ ሰራተኞች አስፈላጊ ስልጠና መሆኑን በመረዳት ከኮሚሽኑ ማኔጅመንት ጋር በመነጋገር ይህን ስልጠና እንዲሰጥ መደረጉን ገልጽዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስልጠናው ጠቃሚ እንደነበር በመግለጽ ከስልጠናው ያገኙትን ልምድና ዕውቀት ወደ ተግባር እንደሚለውጡት እና እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል፡፡

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *