photo_2023-12-18_20-49-31

 ኮሚሽኑ ቅንጅታዊ ሃብት አሰባሰብ  ስልጠና እና JISRA ፕሮጀክት የስራ ሪፖርት አካሄደ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ቅንጅታዊ ሃብት አሰባሰብ  ስልጠና እና የጋራ ተነሳሽነት ለስትራቴጂካዊ ሃይማኖታዊ ተግባር (JISRA) ፕሮጀክት የስራ ሪፖርት  በሀዋሳ ሮሪ ሆቴል  ታህሳስ 8 /2016 ዓ.ም አካሄደ፡፡

ስልጠናውን የኮሚሽኑ የሰው ኃብት እና ኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምሩ ዘለቀ  በጸሎት   ያስጀመሩ ሲሆን እንዲሁም የ JISRA  ፕሮጀክት አስተባባሪ  አቶ  እንዳለ ወ/ሰማያት የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል። አቶ እንዳለ በሮሜ ምዕራፍ 12 ቁጥር 1-2 ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አንብቦ ባለድርሻ አካላት ሰውነታቸውን ሕያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ እና ይህም በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው የተቀደሰ ሕይወት እንዲኖሩ ጥሪውን አስተላልፎል፡፡ የ JISRA የፕሮጀክት ሥራ ሪፖርት  እና ፕሮጀክቱ አሁናዊ ሁኔታ  ለተሳታፊዎች  በዕለቱ ቀርቧል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር  ተፈራ ተሎሬ  ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኮሚሽኑ በመላ ሀገሪቱ የልማታዊ ፕሮግራሞቹን ለችግረኞችና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ ደህንነት እየሰራ እንደለ ገለፃ አድርገዋል። አያይዘውም ኮሚሽኑ ከ50 ዓመታት በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ከውጭ ለጋሾችና ከውስጥ በሚያገኛቸው ድጋፍ በመታገዝ በዋናነት በውሃ፣ጤናና ንፅህና፣ትምህርት፣በኑሮ እና የአደጋ መከላከልና መልሶ ማቋቋም፣ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ውጤታማ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን  ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑም በአሁኑ ጊዜ የተለያዮ ዘመናዊ አማራጮችን በመጠቀም  ቅንጅታዊ ሃብት ማሰባሰብ መጀመሩን የገለጹት ዶክተር ተፈራ   ይህም ስራ  ኮሚሽኑ የፋይናንስ ክፍተቶችን ለማጥበብ፣ ስልታዊ በሆነ መንገድ የኮሚሽኑን የገንዘብ ምንጭ ለማጠናከር እና ድጋፍ እና ልማት የሚፈልጉ የደሃ ማህበረሰብ ክፍሎችን ሕይወት  ይበልጥ በቀጣይነት ተጠቃሚ ለማድረግ ሊንከተል የሚገባ  አስፈላጊ አማራጭ ነውም ብለዋል፡፡

 በዚህም መሰረት በጎ ፍቃደኞች፣ ግለሰቦች እና ማንኛውም ለጋሽ  ኮሚሽኑ በመቻቸው የሃብት ማሰባሰቢያ ስልቶች ማለትም በቴሌብር፣ በአዋሽ ባንክ አካውንት ቁጥር 1426 እንዲሁም ብርሃን ባንክ አካውንት ቁጥር 1426 እና ሌሎች መንገዶችን እንዲለግሱ እና ድሆችን በፍቅር ከኮሚሽኑ ጋር እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅረበዋል፡፡ ከዝህ በተጨማሪ ኮሚሽኑ ከበርካታ ምንጮች ሃብትን በማሰባሰብ ድሆችን እና ማህበረሰቦችን ለመደገፍ እንዲሁም ዘላቂ ማህበረሰብን ያማከለ የልማት ፕሮግራሞችን እና ፕሮጀክቶችን ለማካሄድ እና ዘላቅ ማህበረሰብ ቶኮር ልማቶችን የሚሰራበትን ሁኔታ አጠናክሮ መስራቱን እንደሚቀጥል እና አሁንም በስፋት እየሰራ መሆኑን ኮሚሽነር ዶክተር ተፈራ ተሎሬ ተናግረዋል።

በኮሚሽኑ የሰብአዊ እርዳታና ሰላም ግንባታ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ አብረሃም አለምቦ የቤተክርስቲያኒቱን እና የልማት ኮሚሽኑን የልማት እና ቅንጂታዊ አሰራረን ታርካዊ ሂደት ለተሳታፊዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱ  ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሁለንተናዊ አገልግሎት ጉዞ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል። በተጨማሪም ቅንጅታዊ አሰራራ እና ሀብት አሰባበሰብ ዙሪያ በተመለከተ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ፣ ያለንን ዕምቅ ሀብት እና ድርጅታዊ ሥርዓቶች በሚገባ  ማወቅ እና ወደ ስራ ማግባት እንደሚያስፈልግ እና ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት  አብራርተዋል።

ይህን ግልጽ አላማ እና ግብ ለማሳካትም ቁርጠኝነት፣ ወጥነት፣ ተጠያቂነት፣ አንድነት፣ ታማኝነት እና ሌሎች ለጋራ ስራ አስፈላጊ የሆኑ እሴቶችን መከተል ብዙ ሰዎችን ለማዳረስ እና የቤተክርስቲያንን አፈጻጸም ለማሳደግ ድርጅታዊ ጥረቶችን ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ ናቸው ያሉት ስሆን ይህንንም ለማሰካት ኮሚሽኑ ለባለድርሻ አካላት አብረው እንድሰሩ እና  ህብረተሰቡን  በአሳታፊነት መርዳት የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታን መፍጠሩንም ገልጸዋል።

  አብረሃም ከለጋሽ ድርጂቶች በሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ  እረዳታ እና ልማት የሚፈልገውን እና እያደገ የመጣውን የማህበረሰባችንን ፍላጎት ማሳካት የማይችል መሆኑን አብራርተዋል። ለዚህም ነው ኮሚሽኑ የተቸገሩትን ማህበርሰብ ለመርዳት አሳታፊ፣ የተቀናጀ የሀብት ማሰባሰብያ ሞዴል ያዘጋጀ። ስለዚህም በቤተክርስቲያኒቱ ያለውን የሰው ሀብት እና እምቅ ሃብት በመጠቀም ለማህበረሰባችን ሁለንተናዊ ልማትና እድገት ማስራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም በቅንጅት መስራት ከመቼውም በላይ አስፈለጊ ነውም ብለዋል፡፡

አቶ ዲንቁ ሹሚ የኮሚሽኑ የላይቨሊሁድ እና ሪዚሊያንስ መምሪያ ኃላፊ የእርዳታ እጆች ችግር ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች መድረስ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም ኮሚሽኑ ይህን ታሳቢ በመድረግ ነው ይህን ቅንጅታዊ የሃብት ማሰባሰብ ስራ የጀመረው፡፡ ይህም እየመጡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ኮሚሽኑ በማቻቻል ወደ ስራ እንዲያስገባ እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ ይረዳልም ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሚሽኑ  አድስ ፕሮጀክት ወደ ትግበራ ሊገባ እንደሆነ እና  የፕሮጀክት አጠቃላይ ሁኔታን እና የሚሰራቸው ስራዎችም ለተሳታፍዎች  አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን፣ የጋራ ቦርዶች እና ከፍተኛ አመራሮች በጋራ እ.ኤ.አ October 9/ 2023 በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በኩሪፍቱ ማዕከል የቅንጅታዊ አሰራር እና ሀብት ማሰባሰብያ አውደ ጥናት ማድረጋቸው የሚታወስ ስሆን በዞን ደረጃ ያሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር የሚወክሉ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ መሪዎች በዓውደ ጥናቱ ስልጠና እና ምክክር መድረክ ላይ  ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ በስልጠናው  በተደረጉ ገለጻዎች እና አላማዎች ላይ አስተያየታቸውን እና ሃሳባቸውን በአዎንታዊ መልኩ ያንፀባረቁ ሲሆን ስልጠናውም በመጋበ ሙላቱ ማሴቦ በጸሎት ተጠናቋል።

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *